በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተቀሰቀሰው አዲስ ኢቦላ ቫይረስ ሳቢያ በትንሹ የ15 ሰዎች ህይዎት አለፈ።
ቫይረሱ መኖሩ የተረጋገጠው በ34 ዓመቷ ነፍሰ ጡር ላይ እንደሆነም የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በተያዘው ወር ወደ ሆስፒታል ተወስዳ ኢቦላ ቫይረስ እንዳለባት ይፋ ሲደረግ የተለያዩ ምልክቶች ታይተውባታል ነበርም ተብሏል።
ትኩሳት እና ተደጋጋሚ “ማስመለስ” በአዲስ መልክ የተቀሰቀሰው ኦቦላ ቫይረስ ምልክቶቹ ሆነዋል። ከጥቂት ሰዓታት በኋላም በዚሁ ቫይረስ ህይወቷን ባጣችው እናት ላይ ያልቆመው ቫይረስ ከ15 በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል ብሏል ሚኒስቴሩ።
በማዕከላዊ አፍሪካ በተለይም በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለ16ኛ ጊዜ ቫይረሱ ሲቅሠቀስ እንደሆነም ባለሙያዎች ያስረዳሉ። በማዕከላዊ ካሳኢ ግዛት 28 ሰዎች በቫይረሱ ሳይያዙ እንዳልቀሩም ተመላክቷል።
የዓለም ጤና ድርጅትም ቫይረሱ ሳይስፋፋ ለማስቆም በቁርጠኝነት ስራውን እንደሚከውንም አስገንዝቧል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












