እንግሊዛዊው አማካኝ በልምምድ ሜዳ ላይ ባጋጠመው የጡንቻ መሳሳብ ጉዳት በትንሹ ለሶስት ሳምንታት ከጨዋታ ውጪ መሆኑን ክለቡ አስታውቋል።
አዳም ዋርተን የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከአንዶራ እና ሰርቢያ ላለበት ጨዋታ ጥሪ ተደርጎለት የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ላይ ከውድድሩ ውጪ መሆኑን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል። የ21 አመቱ ተጫዋች ከዚህ ቀደም ባለው የጉዳት ታሪክ ቶሎ የሚያገግም ቢሆንም፤ ፓላስ የማገገሚያ በቂ ጊዜ ሊሰጠው እንደሚፈልግ ተነግሯል።
ክሪስታል ፓላስ ከዋርተን በተጨማሪ ኢስማኢል ሳርም በተመሳሳይ በመጎዳቱ አገልግሎቱን አያገኝም። ሴኔጋላዊው ሳር እንደ ዋርተን ሁሉ ሃገሩ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ደቡብ ሱዳን ከምታደርገው ጨዋታ ውጪ ሆኗል።
በተጫዋች ጉዳት እና ሽያጭ የቡድን ስብስባቸው የሳሳባቸው አሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር፤ ብስጭታቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ሲናገሩ ተሰምተዋል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












