ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ሀሽታጎችን በመጠቀም ለሀገራቸው አምባሳደር መሆን ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናገሩ፡፡
ዓለም አቀፍ የጥናት ተቋማት በፈረንጆቹ 2030 በዓለም አቀፍ ደረጃ የቱሪዝም፣ የፋሽን ኢንዱስትሪ፣ የስብሰባ መስተንግዶና የባህላዊ ምግቦች ጉብኝት የ1 ትሪሊየን ዶላር ገበያ እንደሚሆን ይጠቁማሉ።
የሀገራት ዋናው ጥያቄ “ታዲያ ያለኝን ሀብት ገልጬ፣ መንዝሬ የዚህ ገበያ ተቋዳሽ ለመሆን ምን ማድረግ አለብኝ” የሚል ሲሆን፤ ይህም የመንግስታት ትልቅ ተልዕኮ ነው፡፡
በዲጂታል ዓለም ውስጥ የንቁ ዜጋ ኃላፊነትና አንደኛው የተሳትፎ አይነት ደግሞ ሀገሬ የዚህ ተቋዳሽ እንድትሆን ያላትን ሀብት ለዓለም እንዴት ላሳይ፣ ላሳውቅ፣ እንዴትስ ግንዛቤ ልፍጠር የሚለው ይሆናል ነው ያሉት፡፡
ለዚህም ከታች የተዘረዘሩትን ሀሽታጎች በመጠቀምና በማሳደግ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው አምባሳደር መሆን ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ኃላፊዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
1ኛ. #VisitEthiopia
የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብቶች፣ ቅርሶች፣ ባህልና መልክዓ ምድሮች ያስተዋውቃል፣ የሀገራችንን ዓለም አቀፋዊ ገጽታ እንደ ልዩ አፍሪካዊ መዳረሻ ያሳድጋል።
2ኛ. #buyethiopian እና #madeinethiopia
የኢትዮጵያን ምርቶች ከባህላዊ የፋሽን አልባሳት፣ ቡና እና ዕደ-ጥበብ እስከ አየር መንገድ እና ግብርና ውጤቶች ያስተዋውቃል፣ ኢኮኖሚውን ይደግፋል፣ የወጪ ምርትን ያሳድጋል እንዲሁም የምርት ስም (brand) ኩራትን ይገነባል።
3ኛ. #MeetInEthiopia
ኢትዮጵያን በአጠቃላይ እና አዲስ አበባን ጨምሮ በለውጥ ላይ ያሉ ከተሞቿን ለዓለም አቀፍ ዝግጅቶችና ኹነቶች ማዕከል የመሆን እና የማስተናገድ አቅሟን እና በአፍሪካ ዲፕሎማሲ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ትብብር ያላትን ሚና ያስተዋውቃል።
የኢትዮጵያን የተለያዩ ባህላዊ ምግቦች በማጉላት፣ የምግብ አሰራር ቱሪዝምን በማስተዋወቅ፣ የሀገራችን የምግብ ጣዕሞችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንዛቤን ይፈጥራል።
እንደ ግብርና፣ ኢነርጂ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ቱሪዝምና ቴክኖሎጂ ባሉ ዘርፎች የሀገሪቱን ሰፊ የኢንቨስትመንት እድሎች ያስተዋውቃል።












