በቶማይ መኮንን
August 2, 2025
የዬክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በሩሲያ ጥቃት አድርሰው ሶስት ሰዎች መሞታቸውን የሩሲያ ባለሰልጣናት አስታወቁ፡፡ ጥቃቱ የደረሰው በኢንዱስትሪ እና መኖሪያ አካባቢዎች ሲሆን ሮስቶቭ፣ ሳማራ እና ፔንዛ በሚባሉ ቦታዎች በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱም ነው የተገለጸው፡፡

ዛሬ ማለዳ የዩክሬን የሰው አልባ አውሮፕላን ማዕበል በሩሲያ ግዛቶ መድረሱን እና ለዚህም የአጸፋ ምላሽ የሩሲያ ሀይሎች መስጠታቸውን ከአከባቢው የሚወጡ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡
የሞስኮ ወታደራዊ ባለሰልጣናት እንደገለጹት ከዩክሬን የተላኩትን 112 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ማክሸፉቸውን ነው፡፡ ዩክሬን ለበርካታ ወራት በሩሲያ ግዛቶች ላይ ከባድ ጥቃት እያደረሰች ሲሆን ሩሲያም የአጸፋ መልስ እየሰጠች ትገኛለች::

ሶስት ዓመታትን የተሻገረው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በተኩስ አቁም ስምምነት ይቋጫል ቢባልም ሊቆም አልቻለም ፡፡አሁን ላይ ዩክሬን ያደረሰቸውን ጥቃት ተከትሎ የሩሲያ ሀይሎች የአየር ጥቃት በዩክሬን ላይ እያደረጉ መሆናቸውን ያስነበበው አር ቲ ኒውስ ነው፡፡












