August 2, 2025
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞቹን ረጅም ርቀት ለማጓጓዝ የሚያስችለውን አራተኛውን ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ዛሬ ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም ተረክቧል፡፡

አየር መንገዱ የተረከበው አዲሱ ኤርባስ አውሮፕላን፤ የኢትዮጵያን ገፅታ በአዲስ ዕይታ ከፍ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡ እጅግ ዘመናዊ 4 ኤርባስ A350-1000 እና 20 ኤርባስ A350-900XWB አውሮፕላኖች ባለቤት መሆኑን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












