በሩሲያ የባህር ዳርቻ በ 8.8 ግዙፍ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በሃዋኢ 4ft (1.2m) የሚለካ የሱናሚ ማዕበል ተከስቷል፡፡
በታሪክ ከተከሰቱት ከባድ የመሬት መንቀጥቀጦች አንዱ በሆነው በሩሲያ ምሥራቃዊ የካምቻትካ ግዛት በተከሰተው በዚህ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በሃዋኢ፣ በአንዳንድ የአሜሪካ ምዕራባዊ የባህር ዳርቻ እና ጃፓን የሚኖሩ ማህበረሰቦች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ተሰቷቸው ነበር።
የሃዋኢ ግዛት አስተዳዳሪ ጆሽ ግሪን ሰዎች የመልቀቂያ ትዕዛዞችን እንዲተገብሩ እና እንዲረጋጉ የጠየቁ ሲሆን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካውያን ለማስጠንቀቂያዎች ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስበዋል።
በጃፓን 1.9 ሚሊዮን ሰዎች የመኖሪያ አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያዎች ተሰቷቸዋል፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ-ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












