በጥቃቱ አንዲት እቃ አጓጓዥ መርከብ ስትሰጥም የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል በየመን ሃውቲ ቡድን በኩል የተለቀቀ ሲሆን በቅርብ ርቀት የሃውቲ አማጽያንም በማጂክ ባሕር ላይ ሲንቀሳቀሱ ይታያል፡፡
ቡድኑ መርከቧ ከእስራኤል ጋር የሚሰራ ድርጅት ንብረት እንደሆነች የተናገረ ቢሆንም ባለቤቶቹ ግን ከቱርክ ጋር እንጂ ከእስራኤል ጋር አብረው እየሰሩ እንዳልሆነ አረጋግጠዋል፡፡ የሚሳይል እና ድሮን ጥቃቱ ከመድረሱ በፊት በመርከቡ ውስጥ የነበሩ ሰዎች እንዲወጡ ተነግሯቸዋል ቢባልም ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች መሞታቸውን ግን በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
ለደረሰው ጥቃት የየመን ሃውቲ ቡድን ኃላፊነት እንደማይወስድ የገለጸ ሲሆን በጋዛ ያለው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህም ቡድኑ ከ100 በላይ ተጓዥ መርከቦች ላይ ጥቃት ማድረሱ ነው የተገለጸው፡፡ የቀይ ባሕር አካባቢ እጅግ የተጨናነቀ እና ተደጋጋሚ ጥቃቶች የሚሰሙበት መሆኑን የዘገበው አልጄዚራ ነው፡፡
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












