። ። ። ። ። ። ። ። ። ።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የስፖርቲንግ ሊዝበኑን ተጫዋች ቪክቶር ዮከሬሼን ለማስፈረም ንግግር መጀመሩንና በቅርቡ ሊያስፈርመው እንደሚቼል ተገለጸ።
መድፈኞቹ ከተጫዋቹ ጋር አዲስ ንግግር የጀመሩ መሆናቸው ታዋቂው የስፖርት ተንታኝ ፋብሪዞ ሮማኖ ነው የገለጸው ። ከስፖርቲንግ ለመልቀቅ ፍላጎት ያለው ዮኬሬሽ፣ ከቡድኑ ጋር ልምምድ እያደረገ እንዳልሆነም ተዘግቧል።
በኮንትራቱ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረሳቸው የተገለጸ ሲሆን፣ የስፖርቲንግ ፍላጎትም ተጫዋቹ አርሰናልን እንዲቀላቀል ነው ተብሏል። እየተደረገው ያለው ንግግር በቅርቡ ወደ ተግባር ተለውጦ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ተጫዋቹን ሊያስፈርመው ይችላል ነው የተባለው።












