። ። ። ። ። ። ። ። ። ።
የብሪክስ ጥምረት ዓባል አገራት ጉባዔ በሪዮ ደ ጀነሪዮ ብራዚል ተጀምሯል፡፡
ይህ ግዙፍ መድረክ 4,000 ተሳታፊዎችን ከ37 አገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ያሰባሰበ ሲሆን፣ ቁልፍ ዓለም አቀፍ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
17ኛው ዓመታዊ የብሪክስ ጉባዔ ትላንት እሁድ በተለዋጭ ፕሬዚዳንቷ ብራዚል ሲጀመር በርካታ ጉዳዮችን ግም
ት ውስጥ አስገብቷል።
የሁለት ቀናቱ ጉባዔ በሁለንተናዊ ትብብር፣ በተለያዩ የፕላኔቷ ጉዳዮች እና አስተዳደራዊ ሁኔታዎች ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡
ብራዚል በዚህኛው ዓመት ጉባዔ ላይ ስድስት የትኩረት ነጥቦችን ይፋ ያደረገች ሲሆን:- ዓለም አቀፍ የጤና ትብብር፣ ንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ፋይናንስ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤ አይ) አስተዳደር፣ የሁሉን አካታች ሰላም እና ደህንነት ለውጥ እንዲሁም በብሪክስ ውስጥ የተቋማት እድገት ይገኙበታል፡፡
ህብረቱ በ2006 በብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና
ቻይና “በብሪክ” ስም ከተቋቋመ በኋላ ደቡብ አፍሪካ በ2010 ጥምረቱን ስትቀላቀል “ብሪክስ” መሆኑ ይታወሳል።
በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ አረብ ኤሚሪቶች እና ኢንዶኒዠያ አዳዲስ የጥምረቱ ዓባል አገራት ሆነዋል።
ዘገባው የአር ቲ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












