“ዶዶ ማያና” በሚል የቅጽል ስሙ የሚታወቀው የ61 ዓመቱ ታሪካዊ ተጫዋች፣ ለረዥም ጊዜያት በህመም ሲሰቃይ ቆይቶ ዛሬ ህይወቱ እንዳለፈ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ፒተር ሩፋይ ለ20 ዓመታት በዘለቀው የእግር ኳስ ህይወቱ ለቤልጂየም፣ ኔዘርላንድ፣ ፖርቱጋል እና ስፔን ክለቦች ተጫውቷል። ሎከረን፣ ቤቨረን፣ ጎ ኤሄድ ኢግልስ እና ዲፖርቲቮ ላኮሩኛ ተጫዋቶ ካሳለፈባቸው ክለቦች መካከል ናቸው።
በአውሮፓውያኑ 1994 የአፍሪካ ዋንጫን ያነሳው እና ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ የተሳተፈው የታሪካዊው የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ አካልም ነበር።
በ ይበልጣል ሰውነት
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












