የሰሜን አየርላንዱ ክለብ ግለናቨን አጥቂ ክሪስቶፈር አትኸርተን ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ ፊርማውን አኑሯል።
የ16 ዓመቱ ታዳጊ በመስከረም 2022 በ13 ዓመት ከ329 ቀን ዕድሜው ለግለናቨን ዋናው ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን በማድረግ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቦ ነበር። በ14 ዓመት ከ191 ቀን ዕድሜ በስኮትላንዳዊው የቀድሞ የዎልቭስ ተጫዋች ጆርዳን አለን ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ነበር ያሻሻለው።
አተኸርተን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሰሜን አየር ላንድ ፕሪሚየርሺፕ 10ኛ ደረጃን ይዞ ላጠናቀቀው ግለናቨን መደበኛ ተሰላፊ ነበር። የመጀመሪያ ጎሉን በመጋቢት ወር አስቆጥሯል።
ክለቡ በኤክስ ገጹ ላይ ባሰፈረውም መልዕክት፣ “የአካዳሚ ፍሬያችን ክሪስ አርተን ለቼልሲ ፊርማውን ለማኖር ክለባችንን ለቋል፣ መጪው ጊዜ የስኬት እንዲሆንለት እንመኛለን፣ ክሪስ አትኸርተን አሁንም ሰማያዊ ቀለም” ብሏል።
በይበልጣል ሰውነት
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












