በተደራራቢ ጉዳቶች ምክንያት በተጠበቀው ልክ መጓዝ የተሳነው ቤልጂየማዊው ከቆጶሮሱ ክለብ አኖርቶሲስ ጋር ባለፈው ዓመት ከተለያየ በኋላ ክለብ አላገኘም።
ሙሶንዳ ጁኒየር “ራይዚንግ ቦለርስ ፖድካስት” ላይ ቀርቦ ጫማ መስቀሉን ይፋ አድርጓል። የአጥቂ አማካኙ የቼልሲ ወጣት ቡድንን በ2012 ነበር ከአንደርሌክት የተቀላቀለው። የምዕራብ ለንደኑ ክለብ በወቅቱ ለ16 ዓመቱ ተስፈኛ ተጫዋች ዝውውር 2.5 ሚሊዮን ዩሮ ከፍሏል።
ሙሶንዳ ጁኒየር በቼልሲ ወጣት ቡድኑ ውስጥ ሳለ “የቤልጂየም ታላቁ ባለተሰጥኦ” የሚል ሙገሳ ቢቸረውም ለዋናው ቡድን ከሰባት ጨዋታዎች በላይ ማድረግ አልቻለም። ስታምፎርድ ብሪጅን በ2022 ከመልቀቁ በፊት ለሪያል ቤቲስ፣ ሴልቲክ እና ቪትስ አርንኸም ክለቦች በውሰት ዉል ተጫውቷል።
በተደራራቢ ጉዳቶች ሲፈተን የኖረው ቻርሊ ሙሶንዳ ጁኒየር በስፔኑ ሌቫንቴና በቆጶሮሱ አኖርቶሲስ ለአጭር ጊዜያት ያህል ካሳለፈ በኋላ በ28 ዓመቱ ጫማ መስቀሉን ይፋ አድርጓል። ተጫዋቹ ከቼልሲ መልቀቁ በስነ- ልቦና እንደገደለው “ለራይዚንግ ቦለርስ ፖድካስት” ተናግሯል።
በ-ይበልጣል ሰውነት












