የውሃ ሰማያዊዎቹ ግብ ጠባቂ በያዘነው የክረምት የዝውውር መስኮት ክለቡን ይለቃሉ ከተባሉ ተጫዋቾች አንዱ እንደነበር አይዘነጋም።
በክለቦች አለም ዋንጫ እየተጫወተ የሚገኘው ኤደርሰን፣ በሲቲ ስለሚኖረው ቆይታ ተጠይቆ “ተጨማሪ አመታትን በክለቡ እቆያለሁ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። “የኔን ቆይታ በተመለከት እየተዘገበ የሚገኘው ሁሉ ሃሰት ነው” ያለው ብራዚላዊ ተጨማሪ ትልልቅ ስኬቶችን ከቡድኑ ጋር ማሳካት እንደሚፈልግ ተናግሯል።
ተጫዋቹ ይህንን ይበል እንጂ ከሳዑዲ አረቢያ ክለቦች ጋር ስሙ በስፋት ሲያያዝ መቆየቱ እና ወኪሎቹም ዝውውሩን በተመለከተ ሲደራደሩ እንደነበር አይዘነጋም። ማንችስተር ሲቲም የፖርቶውን ግብ ጠባቂ ዲዬጎ ኮስታን ለማስፈረም በሂደት ላይ እንደነበር ይታወሳል።
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የተጫዋቹ አድናቂ መሆናቸው እና ሲቲም ግብ ጠባቂውን ወደ ኢቲሃድ መውሰዱ አይቀርም እየተባለ ይገኛል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












