የአሜሪካው የስለላና ደህንነት ተቋም (CIA) ዳይሬክተር የኢራን ኑክሌር መርሃ ግብር እጅጉን ወድሟል አሉ።
የተቋሙ ዳይሬክተር ጆን ራትክሊፍ የኢራን የኑክሌር መርሃ ግብር በአሜሪካ ጥቃት ክፉኛ መጎዳቱን የሚያረጋግጥ ታማኝ መረጃ አለኝ በሚል ሀሳባችውን አጋርተዋል። አሜሪካ በፎርዶ እና ናታንዝ እንዲሁም በኢስፋሃን ላይ የረባ ጉዳት አላደረሰችም የሚል አፈትልኮ የወጣ ሰነድ ከጠቆመ በኋላ ነው እንዲህ ዓይነቱ ሀሳብ ከ ሲ አይ ኤ በኩል የወጣው።
በታማኝ የደህንነት ምንጮች ላይ መሰረቱን ያደረገ መረጃ ስለመሆኑ ያስታወሱት ዳይሬክተሩ፣ የኢራን የኑክሌር ጣቢያዎች ወድመዋል ብለዋል፡፡ ማብላያዎቹን ዳግም ለመገንባት በርካታ ዓመታት ኢራንን ያስፈልጋታል ብለዋል ራትክሊፍ፡፡
በእርግጥ ኢራንን ጥቂት ወራት ወደ ኋላ ሊወስዳት ቢችል እንጂ የተፈጸመባት ጥቃት ከባድ አይደለም ተብሏል። አፈትልኮ በወጣው ሰነድ ላይ “የማስተባበያ ዘመቻ በሚመስል” የትራምፕ አስተዳደር ክፍተቱን ለመሙላት እየሰራ ነው በሚልም ይተቻል፡፡
ነገ ከነገ ወዲያ ግልጽ ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅበታልም ተብሏል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ ዘ ሄግ ኒዘርላንድስ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረት (ኔቶ) ጉባዔ ላይ ሆነውም ዓላማችንን በኢራን ላይ አሳክተናል ሲሉ ተደምጠዋል።
ዘ ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው ፡፡
በ-የአብስራ ሚሊዮን












