ኮሚሽኑ ቀሪ ስራዎችን ብሎም ሀገራዊ ምክክር በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ የሚረዱ ምክረሀሳቦች ለመውሰድ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር እየተወያየ ነው።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር አምባሳደር መሐመድ ድሪር በርካታ ዕሴቶች ባሏት ኢትዮጵያ፤ የሃይማኖት ተቋማት ከፍ ያለ አበርክቶ እንዳላቸው ገልጸዋል።

እንደ ሀገር እጅግ መሠረታዊ እና ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያሉ አለመግባባቶችን ዘመኑ በሚጠይቀው መንገድ ለመፍታት የምክክር ምዕራፍ ላይ ስለምንገኝ የሀይማኖት ተቋማት ተሳትፎ መጠናከር እንዳለበት በአጽንኦት ገልጸዋል።
ሁሉም የሀይማኖት ተቋማት በአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ሂደቱ በተወካዮቻቸው በኩል በንቃት በመሳተፍ አጀንዳዎቻቸውን መስጠታቸውን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ ቀጣይ የምክክር ሂደት የተሳካ እንዲሆን ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። ሰላማዊ አገርን ለማስቀጠል እና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት የተጀመረው የምክክር ምዕራፍ ውጤታማ ለማድረግ ለሀይማኖት ተቋማቱ ትብብር ይጠይቃል ነው የተባለው።
የሀይማኖት ተቋማት ለምዕመኖቻቸውን ሰላምን ከመስበካቸው በፊት በቅድሚያ እራሳቸውን ችግሮቻቸውን በምክክር ሊፈቱ እንደሚገባ በውይይቱ ቀርቧል።
በ-ሰላም ይልማ












