በተጠናቀቀው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የተሰናበተው የሳውዝሃምፕተን ግብ ጠባቂ ራምስዴል ወደ ቱርክ ሊያቀና ይችላል ሲል ዘ ሰን አስነብቧል።
የቀድሞው የአርሰናል ግብ ጠባቂ ሳውዝሃምፕተንን ሲቀላቀል ክለቡ ከፕሪምየር ሊግ የሚወርድ ከሆነ በ20 ሚሊዮን ፓውንድ መልቀቅ የሚያስችለው ስምምነት ቀድሞ ተዋውሏል።
የ27 አመቱ እንግሊዛዊ በፕሪምየር ሊግ የመቆየት ፍላጎት ቢኖረውም፣እስካሁን ተጫዋቹን ለመውሰድ ጥያቄ ያቀረበ ክለብ አልተገኘም።
ራምስዴል 100ሺ ፓውንድ ሳምንታዊ ደመወዝ የሚከፈለው መሆኑ ተጫዋቹን ለማስፈረም እንቅፋት እንደሆነ ተዘግቧል።
የ25 ጊዜ የቱርክ ሊግ ሻምፒዮኑ ጋላታሳራይ ራምስዴልን በጥብቅ እየፈለገው ሲሆን፣ ለረጅም ጊዜ ላገለገለው ግብ ጠባቂ ፈርናንዶ ሙስሌራ ተተኪ እንዲሆን ይፈልጋሉ።
ራምስዴል በቀጣይ ቀናት ከፕሪምየር ሊግ ክለቦች የእንውሰድህ ጥያቄ ካልቀረበለት ወደ ቱርክ ይጓዛል ተብሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












