፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ልክ በዚች ቀን እ.ኤ.አ ሰኔ 23 1949 በአሜሪካ የሚገኘው የሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ 12 ሴት ዶክተሮችን አስመርቋል።
ይህ ክስተት በዩኒቨርስቲው ጭምር የህክምና ትምህርትን ለሴቶች የመከልከልን ሒደት የቀለበሠ ነበር። የህክምና ትምህርትን ለመከታተል ለሚፈልጉ ሴት ተማሪዎች እንዲሁም ለአለም የመሻሻል አዲስ እድልን የፈጠረ ነበር።
አሜሪካን የሚገኙ እንዲሁም አብዛኞቹ በአለም ላይ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች ለሴት ልጆች የህክምና ትምህርትን ባይፈቅዱም በቁጥር በጣም ጥቂት ሴት ዶክተሮች ነበሩ።
ነገር ግን በሴቶች ላይ የነበረውን ከፍተኛ ተፅዕኖ የማስወገድ እርምጃን አንድ ብሎ የጀመረው ከዚህ ክስተት በኋላ ነበር።
ይሔ ሁኔታ ለሀርቫድ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ሴት ዶክተሮችን ያስመረቀበት ሲሆን ለአለም ደግሞ በአንድ ላይ በቁጥር ብዛት ያላቸው ሴት ዶክተሮች የተመረቁበት ነው።
በ- ሔርሜላ ተመስገን












