የጣሊያን ሴሪ ኤ የ32ተኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር በወሳኝ ጨዋታ ምሽት ላይ ይጠናቀቃል።
በሴሪ ዓው ሁለተኛ ስፍራ ላይ የሚገኘው ናፖሊ ከመሪው ኢንተር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 4 ለማውረድ በሜዳው ኢንፖሊን ይገጥማል።
ባለፉት 5 ጨዋታዎች ምንም አይነት ሽንፈት ያልገጠመው ናፖሊ፣በወራጅ ቀጠና የሚገኘው ኢንፖሊ የፈትነዋል ተብሎ አይጠበቅም።
የምሽቱ ጨዋታ ወሳኝነቱ ለሁለቱም ቡድኖች ነው። ናፖሊ በዋንጫ ፉክክሩ ለመዝለቅ፣ ኢንፖሊም ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት ነጥቡ ያስፈልጋቸዋል።
ቅዳሜ ዕለት ተጋጣሚውን በማሸነፍ ነጥቡን ያሰደገው ኢንተር በአገር ውስጥ እና በአውሮፓ መድረኮች በውጤታማነት በመጓዝ ለ 3 ዋንጫዎች እየተፋለመ ይገኛል።
በነጥብ መቀራረብ ለይ የሚገኙ ቡድኖችን የያዘው ሴሪ ኤ፣ ከየትኛውም የአውሮፓ ሊግ ከፍተኛ የዋንጫ ትንቅንቅ እየታየበት ነው።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












