። ። ። ። ። ። ። ። ።
በሚይናማር በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የሟቾች ቁጥር ከ3ሺ መሻገሩ ተገለፀ።
ባሳለፍነው አርብ በሚይናማር በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 7 እና 6 ነጥብ 4 የተከሰቱት ሁለት የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች በርካታ ጥፉቶችን አስከትለዋል።
ጥንታዊ አካባቢዎች ፣ የትምህርት ቤቶች፣ በርካታ ህንፃዎችና ሌሎችንም መሰረተ ልማቶች አውድሟል።
በሀገሪቱ በሚገኙ መስጂዶች ውስጥ ፀሎት ላይ የነበሩ ሰዎች ላይ መደርመሱን ተከትሎ 170 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።
ከአውሮፓውያኑ 2021 ወዲህ በወታደራዊ መንግስት የምትመራውና በድህነት ለምትማቅቀው እስያቷ ሀገር ሚያናማር የመሬት መንቀጥቀጥና መዘዙ ሌላ ፈተና ሆኖባታል።
በእርስ በእርስ ጦርነት የምትገኘውን ሀገር የሚመራው ወታደራዊ መንግስት አደጋውን ተከትሎ ከተቃራኒ ሀይሎች ጋር ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ማድረጉን አስታውቋል።
የተኩስ አቁም ስምምነቱ እስከ ሚያዚያ 22 የሚቆይ ነው ተብሏል።
የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው በታይላንድ በተደረመሰው ህንፃ ሳቢያ የሟቾች ቁጥር 22 ሲደርስ 72 ሰዎች መጥፉታቸውም ተነግሯል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












