።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በ20 ተከታታይ ጨዋታዎች ያለመሸነፍ አስደናቂ ጉዞ ላይ የሚገኘው ባርሳ ወሳኙን ራፊኒሃን በምሽቱ ጨዋታ እንደሚጠቀም አሰልጣኝ ሃንስ ፍሊክ ተናግረዋል።
ራፊኒሃ በአለማቀፍ ጨዋታዎች ምክንያት ባለመገኘቱ የካታላኑ ክለብ ከኦሳሱና ጋር በነበረው ተስተካካይ ጨዋታ እና እሁድ ጂሮናን በገጠመበት መርሃግብር ብራዚላዊውን አልተጠቀመም።
በመጀመሪያው ዙር በካታላን የተደረገው ጨዋታ በ 8 ጎሎች የታጀበ ውብ ጨዋታ እንደነበር አይዘነጋም። ሁለቱ ቡድኖች በላሊጋውም ለዋንጫ ፉክክር ውስጥ መሆናቸው የምሽት 4፡30 ጨዋታውን ተጠባቂ አድርጎታል።
አሰልጣኝ ዲዬጎ ሲሞኒ ምንም እንኳን በላሊጋው በሂሳባዊ ስሌት ፉክክር ውስጥ ቢሆኑም ባለፉትን ጨዋታዎች የውጤት መንሸራተት ገጥሟቸዋል።
አትሌቲ የውድድር ዘመኑን ያለ ዋንጫ ላለማጠናቀቅ በሜዳው እና ደጋፊዎቹ ፊት የሚያደርገውን ጨዋታ ክብደት እንደሰጠው ተነግሯል።
የሁለቱ አሸናፊ የሚሆነው ቡድን በፍጻሜው ሪያል ማድሪድን የሚያገኝ ይሆናል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












