፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 16 2017| NBC ETHIOPIA- በአደጋው 42 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የካዛኪስታን የአደጋ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡67 መንገደኞችን እና አምስት የበረራ ሰራተኞችን ኣሳፍሮ ሲበር የነበረው አውሮፕላን የተከሰከሰው ካዛኪስታን ውስጥ ነው።
አውሮፕላኑ ከ2ሺህ ጫማ ከፍታ በላይ ከበረረ በኋላ የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ እያሰማ ነበር፡፡ከአደጋው የተረፉትም ወደ ሕክምና ተቋም እንደተወሰዱ ዴይሊ ሳበህ የተሰኘው ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡












