፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 10 2017| NBC ETHIOPIA- በአስራ አንድ ዓመታት ታሪክ አንድ የኢራን ፕሬዚዳንት በግብፅ ጉብኝት ሲያርደግ የአሁኑ የማስዑድ ፔዜሽኪያን የመጀመሪያው መሆኑ ተነግሯል፡፡
የኢራኑ የዜና ተቋም ኢርና ባሰራጨው ዘገባው የኢራኑ ፕሬዚዳንት በስምንቱ ታዳጊ ሀገራት ወይም ዲ-ኤይት ስብሰባ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላልፋሉ ነው ያለው፡፡
በዚያ ስብሰባ ላይ ስለ ፖለቲካና የሙስሊሙ አለም የምጣኔ ሀብት ብልፅግናና ሌሎች ጉዳዩች ተነስተው ይመከርባቸዋል ነው የተባለው፡፡

የኢራኑ ፕሬዚዳንት ስለ ጋዛ ሰርጥ መልሶ ግንባታና ሰለ ሊባኖስም ጉዳይ መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይሁንና የኢራኑ ፕሬዝዳንት በግብፅ የቆይታቸው ጊዜ አልተገለፀም ነው የተባለው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ












