፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 17 2017| NBC ETHIOPIA -የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፍልስጤም ስደተኞች መልሶ ማቋቋም ኤጀንሲ ወደ ጋዛ ሰርጥ የሚገባው የምግብ እርዳታ ስድስት በመቶ ለሚሆኑ ዜጎች ብቻ የሚውል እንደሆነ ጠቅሶ እርዳታው በቂ እንዳልሆነ አስታውቋል፡፡
በጋዛ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፋ ረሃብ እና ወረርሽኝ መጋለጣቸው የተገለጸ ሲሆን በአካባቢው የሚገኙት የዕለት ምግብ እና ንጹሕ መጠጥ ውኃ ለማግኘት ፈታኝ ሆኖባቸዋል፡፡
በሰሜናዊ ጋዛ ያሉ ተፈናቃዮች በከባድ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ የጠቀሰው ኤጀንሲው ታካሚዎችም መድሃኒት እያገኙ አይደለም ብሏል፡፡
ሰብዓዊ ቀውሱ የተባባሰው ወደ ጋዛ የሚላኩ የምግብ ድጋፍ እና የዓይነት ቁሳቁሶች ዝርፊያ እየተፈጸመባቸው ብሎም በአግባቡ እየደረሱ ባለመሆኑ ነው ሲል ኤጀንሲው ጠቅሷል፡፡
በጋዛው ጦርነት መሰረተ ልማቶች ከመውደማቸው ባሻገር እስከአሁን ከ44ሺህ በላይ ዜጎች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን 105 ሺህ ያህሉ ቆስለዋል ፤ 11ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ይኑሩ ይሙት ሳይገለጽ የደረሱበት አልታወቀም ሲል የዘገበው ሚድል ኢስት ሞኒተር ነው፡፡
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook- https://web.facebook.com/ethiopiannbc/
📌Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት












