፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጥቅምት 23 2017| NBC ETHIOPIA-የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ በተለያዩ አከባቢዎች ያስገነባቸውን የኮንስትራክሽን ግብአቶች ማምረቻ ፍብሪካ እና የመኖሪያ ቤትችን የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት አስመርቋል ።
ለምረቃ የበቁት ህንጻዎች ደረጃቸውን በጠበቀ መንገድ የተገነቡ መሆናቸውን የተገለፀ ሲሆን የመኖሪያ ቤቶቹ ምቾትን ማዕከል አድርገው የተገነቡ መሆናቸው ተጠቁሟል
የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በኮከብ ጽባህ እና በምራቅ አጠቃላይ ትምህርት ቤት አከባቢ የተገነቡ ሲሆን ለኑሮ ምቹ ተድርጎው መገንባቻቸው ተገልጿል ።
የኮከብ ጽባህ ሳይት በ1263 ካሬ ላይ ያረፈ እስከ 148 ካሬ ድረስ ስፋት ያላቸው ዘመናዊ ቤቶች የያዘ ነው።እንዲሁም ባለ ሁለት ብሎክ ሲሆን 13 ወለል ያለው ህንጻ ነው።
በተመሳሳይ የምስራቅ አጠቃላይ ሳይት በ1542 ካሬ ላይ ያረፈ ባለ 13 ወለል ሲሆን 60
ዘመናዊ ቤቶችን የያዘ መሆኑ ተገልጿል ።

ሌላኛው ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የኮንስትራክሽን ግብአት ማምረቻ ማእከል የኮርፖሬሽኑን የኮንስትራክሽን ግብአት ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር ት ጥራት ያላቸውን ግብአቶችን በማማረት በዘርፉ የሚታየውን የግብአት ለመቅረፍ ከፍተኛ አበርክቶ ይኖረዋል ተብሏል ። ግንባታው በአንድ አመት የተጠናቀቀ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን 1 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል ።
በምረቃ መርሃ ግብሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሀይ ጳውሎስን ጨምሮ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ፣ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook – https://www.facebook.com/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












