፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 23 2017| NBC ETHIOPIA- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት ከተማ አቀፍ የገቢ ንቅናቄ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የገቢ ዘርፉን በተመለከተ በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ቢኒያም ምክሩ በቀረበው ሪፖርት ለ2017 በጀት ዓመት ከተመደበው 230 ቢሊዮን ብር 63 በመቶው የመዲናዋን ነዋሪዎች ህይወት ለሚለውጡ ፕሮጀክቶች የሚውል ነው።
ስምንት አዳዲስ የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ የቤት ግንባታ፣ እንደ ትምህርት ቤት እና ጤና ተቋማት ያሉ የማህበረሰብ አገልግሎት መስጫ ከፕሮጀክቶቹ መካከል ስለመሆናቸው የቢሮው ሃላፊ ቢኒያም ምክሩ ተናግረዋል።
ብልሹ አሰራር፣ የቴክኖሎጂ ክፍተት እና የአደረጃጀት ችግርን የመሳሰሉ ጉዳዮች የገቢ ስርዓቱን እየፈተኑት ስለመሆኑ ተገልጿል።
የተሰበሰበው ግብር በሚታዩ ልማቶች ላይ እየዋለ መሆኑን የገለፁት ሃላፊው ግብር ከፋዩ ይሄን ተረድቶ ግብሩን በታማኝነት እንዲከፍል ጥሪ አቅርበዋል።
የተሰጠውን የላቀ ገቢ የመሠብሰብ ሃላፊነት እየተወጣ ስለመሆኑ የሚገልጸው ቢሮው መድረኩ የታቀደውን የ230 ቢሊዮን ብር ገቢ በላቀ ደረጃ ለመሠብሰብ ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።
ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ፣ አስመጪዎች፣ አምራቾች፣ አከፋፋዮች፣ የግብር አምባሳደሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ታድመውበታል።
በመድረኩ የተገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












