Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

September 23, 2024
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram
በአለማችን ለስደተኞች በጣም ውድ ከሆኑት ከተሞች አንዷ ናት፡፡አልፎ አልፎ "ሊዮንዳ" ወይም "ቅዱስ ፖል ዴ ሊዮንዳ" በመባል ትጠራለች የአንጎላዋ ዋና ከተማ ሉዋንዳ፡፡ 
ከአፍሪካ ጥንታዊ የቅኝ ግዛት ከተሞች መካከል እና ከአንጎላ አምስት ሜትሮፖሊታን ከተሞች አንዷም ናት ሉዋንዳ፡፡ በሰሜናዊ አንጎላ በአትላንቲክ የባሕር ዳርቻ ላይ የምትገኘው ይህች ከተማ የአገሪቷ ትልቋ ከተማና ከተጨናነቁ የባህር ወደቦች መካከል አንዷም ጭምር ናት፡፡እንዲሁም የኢንዱስትሪ፣ የባህል እና የፖለቲካ ብሎም የቱሪስት ማዕከልም ናት፡፡ ከተማዋ በአውሮፓያውያኑ አቆጣጠር 1576 በፖርቹጋላዊው አሳሽ ፓኦሎ ዲያስ ዲ ኖቫስ እንደተቆረቆረችና እና በ1627 ፓርፖርቹጋላውያን ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሰፈሩባት ታሪኳ ያስረዳል፡፡ በዚህም የፖርቹጋል ቅኝ ግዛት አስተዳደር ማዕከል ብሎም የባሪያ ንግድ ወደብ በመሆን እስከ 1836 አገልግላለች፡፡ በ1975  ከፖርቹጋል ቅኝ ግዛት ነፃ ስትወጣ የነፃዋ አንጎላ ዋና ከተማ ሆነች። በ21 ኛው ክፍለ ዘመን ከተማዋ ትልቅ የመልሶ ግንባታ ስራ ላይ ስትሆን የከተማዋን ገጽታ በእጅጉ የሚቀይሩ ብዙ አዳዲስ ትላልቅ እድገቶች እየተከሰቱባት ነው፡፡

ሉዋንዳ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላት ሲሆን በሀገሪቱ በጣም ተወዳጅ የቱሪስት መዳረሻ ናት፡፡

ታሪካዊ እና ሰማይ ጠቀስ ፎቆቿ እንዲሁም ሰፋፊ መንገዶቿ ሉዋንዳን ዘመናዊ መልክን ሰጥቷታል፡፡ የሀገሪቱ ትልቅና ዋና የኢኮኖሚ ማዕከል የሆነችው ሉዋንዳ ታሪካዊ ሙዚየሞች ፤ብሄራዊ ፓርኮች ፤ሲኒማ ቤቶች ፤ባህር ዳርቻችን ጨምሮ በርካታ የጎብኚዎች መዳረሻዎችንበውስጧ ይዛለች፡፡በዛሬው የመዳረሻ ሰአታችን ጥቂቶቹን ልንንግራችሁ ወደናል፡፡

ከአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ 40 ኪሜ ወይም 25 ማይል ርቀው ቢጓዙ ቀልብን የሚስብ አስደናቂ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ያለው ውብ ስፍራ ያገኛሉ….ሚራዶሮዳ ሉዋ፡፡ ይህ ስፍራ የተለያየ ቀለም ያላቸው የድንጋይ ክምችቶች ገደል ነው። ሚራዶሮ ዳ ሉዋ ከፖርቱጋልኛ ቃል የተተረጎመ ሲሆን “የጨረቃ እይታ” የሚል ትርጓሜም አለው፡፡

ስፍራው ከጊዜ በኋላ በንፋስ እና በዝናብ ምክንያት በተከሰተው የአፈር መሸርሸር ሳቢያ ዛሬ የምናየው አስገራሚና ልዩ ገጽታን ፈጥሯል፡፡

ስፍራው በርካታ የሀገር ውስጥ ብሎም የውጭ ጎብኚዎች አብዝተው ለማየት የሚመርጡት ማራኪ እይታ ያለው ገደላማ መስህብ ነው፡፡

እንደ ሰይፍ የተሳሉ የሚመስሉት ሸለቆዎቹ እና አስደናቂ መልክዓ ምድሩ ይበልጥ ውበቱ የሚገለጠው ጀንበር ስትጠልቅ ነው ፡፡ ጎብኚዎችም ከጨረቃ በቅርብ ርቀት እንዳሉ እንዲሰማቸው ያደርጋል።

ከሉዋንዳ በቅርብ ርቀት የሚገኘው የሙሱሉ ደሴት ጎብኚዎች ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ የእረፍት ቀናትን ለማሳለፍ የሚመርጡት ሌላኛው ተወዳጅ ውብ ስፍራ ነው ፡፡ ከሉዋንዳ በስተደቡብ የሚገኘው የሙሱሉ ደሴት በአንጎላ ታዋቂ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡ ይህ ባህር ዳርቻ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ የተዘረጋ ሲሆን በግምት 30 ኪ.ሜ ርዝመት እንዳለው ይነገራል፡፡ በነጭ አሸዋማ የባህር ዳርቻዎች እና ንጹህ ውሃ የሚታወቀው የሙሱሎ ደሴት ለተፈጥሮ አፍቃሪዎች እና የውሃ ስፖርት ወዳዶች መዳረሻ ነው፡፡ በጀልባ ሽርሽር ለመዝናናት  ፤ የባህር ዳርቻ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ እንዲሁም የውሃው ጥልቀት አነስተኛ በመሆኑ እንደልብ ለመዋኘት አመቺ ነው፡፡ ማረፍ  ከፈለጉም ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች እና ምግብ ቤቶች በብዙ አማራጭ ያገኛሉ፡፡ በዚህም የቱሪስቶች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡

በሉዋንዳ ከተማ በሞሮ ዳ ክሩዝ ውስጥ የሚገኘው ብሔራዊ የባርነት ሙዚየም አንጎላውያን ለ500 ዓመታት በባርነት የቆዩበትን ፤ ተጎጂዎችን ለማሰብ እና ለዘመናት የተፈጸሙትን አስከፊ ድርጊቶች በጋራ ለማስታወስ የተዘጋጀ ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ1997 የተመረቀው ይህ መታሰቢያ ሙዚየም በባሪያ ንግድ ወቅት ጥቅም ላይ የዋሉ ውድ ዕቃዎችን ፤ ፎቶግራፎችን ይዟል። በተጨማሪ ብሔራዊ የባርነት ሙዚየም ብዙ መስህቦች አሉት፡፡ በሀገሪቱ የነበረውን የባሪያ ንግድ ታሪክ በመግለጽ የሚያሳዩበትን የቲያትር ተውኔቶች፤ የግጥም ፣ የሙዚቃ ፤ የአውደ ጥናቶች የሚቀርቡበትና የሚታዩበትም ስፍራ አለው ፡፡

በአንጎላ የባሪያ ንግድን እና የግዳጅ ሥራን ለማስታወስ የተመሰረተው ይህ ሙዚየም በአሁኑ ጊዜ በአንጎላ በብዛት ከሚጎበኙ ሙዚየሞች አንዱ ሲሆን በወር እስከ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ጎብኚዎች ወደ ሥፍራው ያቀናሉ፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

የሲሪላንካ ምርጫ

Next Post

በተለዋዋጭ የአየር ንብረት ለቀዳማይ ልጅነት መሠረት መጣል

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post
በተለዋዋጭ የአየር ንብረት ለቀዳማይ ልጅነት መሠረት መጣል

በተለዋዋጭ የአየር ንብረት ለቀዳማይ ልጅነት መሠረት መጣል

የ2017 የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር የሀይማኖት አባቶች፣የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮች ከጸጥታ አካላት በተጨማሪ ሀላፊነታቸው እንዲወጡ ተጠየቀ

የ2017 የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር የሀይማኖት አባቶች፣የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮች ከጸጥታ አካላት በተጨማሪ ሀላፊነታቸው እንዲወጡ ተጠየቀ

ኢትዮ ቴሌኮም “ኮፐር ስዊች ኦፍ ” የተሰኘ ኢኒሼቲቭ ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም "ኮፐር ስዊች ኦፍ " የተሰኘ ኢኒሼቲቭ ይፋ አደረገ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?