፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጳጉሜ 04 2016| NBC ETHIOPIA- የሩሲያ ባለስልጣናት ትናንት በሰጡት ማብራሪያ በስተምስራቅ ዩክሬን የምትገኘውን የፓክሮቨስክ ከተማ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠራቸውን አስታውቋል፡፡
ከተማዋ በጦርነት ሂደት ስልታዊ እንቅስቃሴ የሚደረግበት መሆኗም ነው የተገለፀው፡፡ የሩሲያ ጦር አሁንም ወደፊት እየገሰገሰና በሁሉም ግንባሮች የዩክሬንን ሀይል ለመስበር ብርቱ ውጊያ መክፈቱም ነው የተነገረው፡፡
የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ በሰጠው መግለጫው በጦር ሀይሉ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር የዋለችዋ ከተማ ጠቃሚ የባቡርና የአስፋልት መስመር ዋና መቆየት መሆኗንና ከአስራ አራት ሺ በላይ ህዝብ የሚኖርባት እንደሆነች ነው ያስታወቀው ዘገባው የኢንዲያቱዴይ ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












