፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጳጉሜ 04 2016| NBC ETHIOPIA- የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ለስራ ጉብኝት ዛሬ ጎንደር ከተማ ገብተዋል፡፡
የስራ ኃላፊዎቹ ጎንደር ከተማ ሲገቡም በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ አስተባባሪና የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሳው ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘውን ጨምሮ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች በአፄ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ አቀባበል ተደርጓላቸዋል።

በጎንደር ከተማ ቆይታቸው በፌደራል መንግስት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጎንደር ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
📌Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












