
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማስተናገድ ብቃት በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በመደበኛ ጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄና አስተያየቶቻቸውን አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ኢትዮጵያ የቱሪዝም ጸጋና ሀብቷን በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቷን ለማሳደግ እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል።
መንግሥት ባለፉት ዓመታተ ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት በርካታ የቱሪዝም መሰረተ ልማቶች መገንባታቸውንም አመልክተዋል።
በቱሪዝም ዘርፉ በተከናወኑ ስራዎችም የሚጨበጡ ውጤቶች መገኘታቸውን ተናግረዋል።
ከነዚህ ውስጥ አንዱ ኢትዮጵያ በርካታ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች የሚካሄዱባት ሀገር እየሆነች መምጣቷን ጠቅሰዋል።
በአዲስ አበባው የአፍሪካ የጤና ጉባኤ ላይ 35 ሺህ ገደማ ልዑካን በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ወቅት የተለያዩ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን የማስተናገድ የሚቻልበት አቅም መገንባቱን አብራርተዋል።











