Thursday, November 26, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላተ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ -ክፍል ሁለት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላተ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ -ክፍል ሁለት

November 26, 2026
in News, Politics
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

ኢትዮጵያ የፀናቸው በፈተናዎች ውስጥ አልፋ ነው!

ኢትዮጵያ ለዘመናት የዘለቀችው በፈተናዎች ወስጥ አልፋ ነው። ኢትዮጵያ በተደራጁ ሰራዊቶቿ፤ የተባበረ ልብ ባላቸው ህዝቦቿ እንዲሁም ዋጋ ለመክፈል በማይሰሰቱ ልጆቿ አማካኝነት ፈተናዎችን ተሻግራ ስሟን አጽንታ ይዛለች።

መከላከያ ሠራዊትን በሚመለከት

መከላከያ እንደ ቤት ነው። መከላከያን ብቻውን ብንገነባ አይዘልቅም። ኢኮኖሚው እሱን የሚሸከም መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል። መከላከያ በአንድ ምሶሶ መቆም አይችልም። ሁሉም ምሶሶዎች መገንባት አለባቸው። እነዛ ምሶሶዎች ደግሞ የአየሩም፣ የምድሩም የቴክኖሎጂውም ነው። በዚህም በመከላከያ ስትራቴጂ አማካኝነት በሁሉም ምሶሶዎች ሸብረክ የማይል ጠንካራ ሠራዊት እየተገነባ ነው። መከላከያ ቴክኖሎጂን በሚገባ የሚጠቀም ተቋም አድርገነዋል። ይህም በውጤቱ እየታየ ነው።

ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም

ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም ራሷን እንደታላቅ ወንድም በመቁጠር እየሰራች ነው። ይሄ ደግሞ እንዲሁ የሚነገር ሳይሆን በሩዋንዳ፣ በሶማሊያ ፣ በኮንጎ፣ በላይቤሪያ ፣ በደቡብ ሱዳን ተሰልፈን ሞተን በተግባር ያሳየነው ነው። አባቶቻችን አድርገውታል፤ እኛም አድርገነዋል። ይህን በጎ ስራ ለመድገም ነው የምንዘጋጀው።

አድዋ ይደገማል፤ አትሞክሩን!

ኢትዮጵያ በታሪኳ የትኛውንም ሀገር በመውረር አትታወቅም። ወደፊትም ያ ፍላጎት የላትም። ሌሎች ማወቅ ያለባችው ግን ትንሽም ይሁን ትልቅ። ማንም ሰው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መጥቶ ኢትዮጵያን ወርሮ በክብር መመለስ አይችልም። ይሄ በጂኦግራፊ የታጠረ ጉዳይ አይደለም። ማንም ነው ያልኩት። አድዋ ይደገማል፤ አትሞክሩን!

ሠላምና ይቅርታን በሚመለከት

በንግግር በሠላማዊ መንገድ ችግሮችን መፍታት የስልጣኔ ምልክት ነው። ታጋሽነት፣ ቻይነትና ይቅር ባይነትን መላበስ ለሀገር ግንባታ በእጅጉን ያግዛል። ሠላምን የምናስቀድመው የአንድ ቀን እረፍት ለእናቶች ያላትን ጥቅም ስለምናውቅ ነው። ስለ ሀገር የሚከፈል ዋጋ መረር ያለ እውነትን መቀበል ይፈልጋል፤ ከዛ ውስጥ አንዱ ይቅርታ ነው። ይቅርታን የምናስቀድመውም ንግግርና ሰላም ለኢትዮጵያም ለቀጣናውም እጅግ ጠቃሚ ስለሆነ ነው።

ኢትዮጵያን ማወክ ለሚፈልጉ የውጭ ኃይሎች

“ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም” በሚል ስጋት ኢትዮጵያን ለማወቅ የምትፈልጉ ሁሉ፤ ባቄላዋ አድራለችና ከእንግዲህ አትቆረጠምም፤ መተው ነው የሚሻላችሁ! ገና ካደረች የሚል ሳይሆን አሁን አድራለች!

በትጥቅ ለሚንቀሳቀሱ አካላት መልዕክት

መንግስት ራሱን ለማቆየት ሳይሆን የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ ጨክኖ የሚሰራ ነው። እናንተ በያዛችሁት መንገድ መቼውም አይሳካም። ከእናነት በላይ አሻግሮ የሚያቅድ መንግስት ነው። ስለዚህ ይብቃችሁ ተመለሱ ወደ ሠላም ብትመለሱ ይሻላል ነው መልዕክቴ!

የትግራይ ክልልን በሚመለከት

የትግራይ ሕዝብ ትጉ ሰራተኛ ነው፤ ሰላም ወዳድ ነው ግን እድል አላገኘም። በከፍተኛ ሁኔታ ወጣቶችን እየገበሩ እድሜያቸውን የሚያቆዩ ሰዎች ተፈጥረውባቸው ቆይተዋል። እነዛ በሰላም ጊዜ የሚፎክሩ ሰዎች አስገዳይ እንጂ ሟች አይደሉም። የትግራይ ሕዝብ አሁን በሚገባ ነቅቷል።ወደ ሠላማዊ ጉዞው ተመልሷል። በዚህ ውስጥ የእኛ ተግባር የተሟላ ሰላም መመለስ፤ መሰረታዊ አገልግሎት መመለስ፤ የትግራይ ህዝብ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳደር ምርጫ በፍጥነት ማካሄድና የተቸገሩትን ደግሞ ማገዝ ነው።

ሀገራዊ ምክክርን በተመለከተ

በምክክሩ ህገ-መንግስቱን በሚመለከት የቀረቡ ምክረ ሃሳቦችን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የሕግ ባለሙያዎች ላላፉት ወራት ቀን እና ማታ ሲሰራ ቆይቷል። በሚቀጥሉት ጊዜያትም ይህ ጉዳይ የሚጠናቀቅ ይመስለኛል። የእኛ አቋም አራት ዓመት የተለፋበት እያንዳንዱ ሃሳብ መተግበር አለበት የሚል ጽኑ አቋም አለን። በዚሁ መንገድ የሚፈጸም ይሆናል።

ታላቁ የመደመር ስትራቴጂን በሚመለከት

ታላቁ የመደመር ስትራቴጂ፤ ከመንግስት የሚሻገር፤ ከትውልድ የሚሻገር የስልጣኔ ጉዞ ያስፈልጋል በሚል የተዘጋጀ ነው። በቅድሚያ ኢትዮጵያ ሃብታም ናት፤ ዜጎቿ ደግሞ ደሃ ናቸው። ይህን እንዴት መቀየር ይቻላል የሚለውን አጠናን። ሁለተኛ የት መድረስ እንፈልጋለን የሚሉውን የሚቀይሩ ግቦቻችን አስቀመጥን። ሶስተኛ በምን አቅም ነው እዛ የምንደርሰው የሚለውን ይዟል። አቅጣጫችንንም ጥርት አድርጎ ያሳያል። ልማት ከመጣ በኋላ ደግሞ እንዴት እናስተዳድረዋለን የሚለውንም አስቀምጧል። ይሄን ለማድረግ ሀገር የሚገነባባት 15 ሞዴሎች ተቀምጠዋል። ያንን ደግሞ በሃይል ቬክተር አማካኝነት ወደ ብሔራዊ ሃይል ይቀየራሉ። ብሔራዊ ሃይል ደግሞ በኢኮኖሚ አርክ አማካኝነት ካፒታልን ለማምጣትና ለማስተዳደር ይውላል። ስልጣኔን የምንገነባው ለትውልድ ነው። በእኔ እምነት የልጅ ልጆቻችን መሰረቱን ይረግጣሉ። ልጆቻቻን ደግሞ ምሶሰውን ይይዛሉ። የእኔ እና እናንተ ስራ እየገነባን ጣሪያ ላይ መቀመጥ ነው። ይሄ ገንቢ ትውልድ ነው። የሚጠቀሙት ልጆቻችን ናቸው።ለመገንባት መታደል ጥሩ ነገር ነው። ገንብቶ ማሸጋገር ግን ጥበብ ይፈልጋል።

ኤርትራን በተመለከተ

የኤርትራ መንግስት ከተደበቀበት ወጥቶ ከማያውቅበት በራሳችን አውሮፕላን እየወሰድን ጎረቤት ጋር አገናኝተነዋል። ይህን ያደረግነው በጋራ ማደግ እንደምንችል ስለምናምን ነው። ከኤርትራ መንግስት አብረን ለመልማት ከፍተኛ ጥረት አድርገናል። ለምሳሌ ኤሌክትሪክ ስለሚቸገሩ እናስገባላችሁና በኢትዮጵያ ዋጋ ተጠቀሙ ብለናቸው ነበር። ነገር ግን የኤርትራ መንግስት አልፈለገም።መንገድ፣ ወደብ በጋራ እንስራ ብለን ጠይቀን የኤርትራ መንግስት አልፈለገም። ምክንያቱ ደግሞ የኤርትራ መንግስት ለጊዜው መንግስት ነው። ነገር ግን ልማት፣ እድገት የሚል ቋንቋ መዝገበ ቃላቱ ውስጥ የለውም። ልማት ፈጽሞ አይገባቸውም። ይሄ የእነሱ ድክመት ነው። ሰሜን እዝ ሲጠቃ ያሳዩት የመልካም ጉርብትና ባህርይ ደግሞ ይመሰገናል። ነገር ግን ችግሩ የተጀመረው ወደ ትግራይ በመግባት ወጣቶችን መግደል፣ መሰረተ ልማት ማውደምና መዝረፍ ሲጀምሩ ነው። በመጨረሻም የፕሪቶሪያው ውል ሲፈረም የኤርትራ መንግስት ማኩረፍ ጀመረ። አሁን ኬርትራ መንግስት የምንፈልገው ሁለት ነገር አለ። አንዱ የኢትዮጵያን ጠላት ማስታጠቅ፣ ማስታጠቂያ መስመር መሆን፤ ለኢትዮጵያ ጠላቶች መተባባበር አቁሞ። ሁለተኛው ደግሞ ለጋራ ልማት አብረን እንስራ። አብረን ስንሰራ ሃሳቡን፣ ገንዘቡንና ጉልበቱን እኛ እናዋጣለን። ተባባሪ ብቻ እንድትሆኑ ነው የምንፈልገው። ይህን ማድርግ ከቻላችሁ በሰላም አብሮ መኖር ይቻላል። ነገር ግን ሻዕቢያ በማይታረም ስህተት ውስጥ የሚዳክር ሃይል ከሆነ ጥፋቱ ለኤርትራ ነው የሚሆነው።

#የጠሚሩምላሾች

#PMOEthiopia

Source: @NBCEthiopia
Via: NBCEthiopia
Tags: EritreaEthiopiaEthiopian defense forceHouse of People's RepresentativesPM Abiy Ahmed
ShareTweetShare
Previous Post

ኤርትራን በተመለከተ

Next Post

ኢትዮጵያ የባህር በር የምትፈልገው ሌሎችን ለመጉዳት ሳይሆን በጋራ ለማደግ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Related Posts

News

ኢትዮጵያ የባህር በር የምትፈልገው ሌሎችን ለመጉዳት ሳይሆን በጋራ ለማደግ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 26, 2026
1
ኤርትራን በተመለከተ
News

ኤርትራን በተመለከተ

November 26, 2026
4
የኢትዮጵያን ክብር እና ታሪክ አስጠብቆ ማስቀጠል የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#ethiopia

የኢትዮጵያን ክብር እና ታሪክ አስጠብቆ ማስቀጠል የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 26, 2026
8
ባለፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#ethiopia

ባለፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 26, 2026
6
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላተ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ክፍል -1
Economy

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላተ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ክፍል -1

November 26, 2026
6
የኢትዮጵያ እዳ ከከፍተኛ ተጋላጭነት ወደ መካከለኛ ደረጃ ዝቅ ማለቱ የሪፎርሙ ትልቁ ስኬት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#ethiopia

የኢትዮጵያ እዳ ከከፍተኛ ተጋላጭነት ወደ መካከለኛ ደረጃ ዝቅ ማለቱ የሪፎርሙ ትልቁ ስኬት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 26, 2026
7
Next Post

ኢትዮጵያ የባህር በር የምትፈልገው ሌሎችን ለመጉዳት ሳይሆን በጋራ ለማደግ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

ኢትዮጵያ የባህር በር የምትፈልገው ሌሎችን ለመጉዳት ሳይሆን በጋራ ለማደግ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 26, 2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላተ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ -ክፍል ሁለት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላተ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ -ክፍል ሁለት

November 26, 2026
ኤርትራን በተመለከተ

ኤርትራን በተመለከተ

November 26, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

ኢትዮጵያ የባህር በር የምትፈልገው ሌሎችን ለመጉዳት ሳይሆን በጋራ ለማደግ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 26, 2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላተ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ -ክፍል ሁለት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላተ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ -ክፍል ሁለት

November 26, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?