
ሁሉንም ዘርፎች አስተሳስሮ እና አስተባብሮ ሀገራዊ ስልጣኔን ለመገንባት በመንግሥት በኩል ምን ዝግጅት ተደርጓል የሚል ቢገለጽ?
መንግስት ጤናማና ፍትሐዊ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ዘርግቶ የታክስ ግብን እውን ለማድረግ ምን አዳዲስ ስልቶችና እርምጃዎች እየወሰደ ነው? በታክስ አሰባሰብ ሂደት የሚታየውን ሌብነት፣ ብልሹ አሰራር ለመግታትና ጥብቅ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ምን ተጨባጭ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው?
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ከመቅረፍና የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ከማረጋገጥ አንፃር እስከአሁን ያበረከተው አስተዋጽኦ ምንድነው?

የሀገራችን ዕዳ የመክፈል አቅም በአሁኑ ወቅት ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
የውጭ ምንዛሬ ተመን ለውጥ ተከትሎ ለሚነሱ የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት መንግስት የሚሰጠው ማብራሪያ ምንድነው? ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ እየተደረገ ያለው ጥረት ምን ይመስላል?
ኢትዮጵያ በህዝብ ብዛቷ በኢኮኖሚ ስፋቷ እና እድገቷ በቀጣናው አንከር ስቴት እንደሆነች ይታመናል፡፡ የኢትዮጵያ መረጋጋት ሰላም እና እድገት ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት ቀጥተኛ አስተዋጾ ያለው ከመሆኑ በላይ ቀጣናውን ለማረጋጋት ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ሚና እንዳላት ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ በዚህም መሰረት ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተቀባይነት እና ተጽዕኖ ፈጣሪነት በመጠቀም እንደዚሁም ዓለም አቀፍ አቅምን በማስተባበር ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት የማይተካ አስተዋጾ ለማድረግ በመደመር መንግሥት የተያዘው እቅድ ምንድን ነው?

ካለፉት ፈተናዎች ትምህርት በመውሰድ፣ የመከላከያ ሠራዊታችንን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል፣ በመረጃ አቅምና በሀገር በቀል የመከላከያ ኢንዱስትሪ ይበልጥ ለማጠናከር ምን ታቅዷል? አዳዲስ አቅሞች ለሀገራችን የመከላከያ አቅም ምን ስትራቴጂያዊ ብልጫ ያስገኛሉ? በተገኘው ውጤት ሳንረካ ለበለጠ ከፍታ መትጋት የመደመር መንግሥታችን መርህ እንደመሆኑ፣ የመከላከያ አቅም ግንባታችን አሁን የሚገኝበት ደረጃና ቀጣይ ስትራቴጂያዊ ትኩረታችን ምንድን ነው? ለሕዝብ ሊገለጽ በሚችለው መጠን ቢያብራሩልን?











