Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

በ3ኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ የታየው የሚዲያ ውበትና ትብብር

November 10, 2026
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የአፍሪካ ድምፅ፣ የሩሲያ አጋርነትና የጋራ የወደፊት ራዕይ፤ በሞስኮ በተካሄደው 3ኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ በታየው ደማቅ የሚዲያ ድባብ ከተራ የዜና ሽፋን በላይ ትርጉም ነበረው።

ይህ መድረክ ከ46 የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ጋዜጠኞችንና ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ባለሙያዎችን በአንድ ቦታ በማገናኘት ለአፍሪካውያን የጋራ ውይይት፣ የልምድ ልውውጥና የጋዜጠኝነት ትብብር ሰፊ ዕድል ፈጥሯል።

ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ጋዜጠኞች በጉባኤው ወቅት የነበራቸው ተሳትፎ፣ የጋራ ውይይቶችና ቃለ መጠየቆችና አንድ ጠቃሚ እውነታን አጉልተው አሳይተዋል፤ አፍሪካ የራሷን ታሪክ በራሷ ድምፅ የምትናገርበት፣ የራሷን የልማት አጀንዳ የምትቀርጽበትና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የራሷን አቋም የምታሳይበት ጊዜ እየጠነከረ እየመጣ መሆኑን።

የሩሲያና አፍሪካ ታሪካዊ ግንኙነት፤ ከነጻነት ትግል እስከ ዘመናዊ ትብብር

የሩሲያና የአፍሪካ ግንኙነት የዛሬ ጉባኤዎችና የዲፕሎማሲ ውይይቶች ብቻ የፈጠሩት አይደለም። ረጅም ዘመናትን የተሻገረ ታሪካዊ መሠረት ያለው እንጂ። ሩሲያ በተለያዩ ወቅቶች ለአፍሪካ ነጻነት ትግሎች ያደረገችው ድጋፍ፣ በትምህርት፣ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በሰው ኃይል ልማት የነበራት ተሳትፎ በሩሲያ–አፍሪካ ግንኙነት ታሪክ ውስጥ የሚጠቀሱ
ናቸው።

አፍሪካ በዓለም ገበያ፣ በኢንዱስትሪ፣ በላቦራቶሪ፣ በምርምር ተቋማትና በዓለም ኢኮኖሚ ውሳኔዎች ውስጥ የራሷን ድርሻ ለማሳደግ በምታደርገው ጥረት አጋርነትና የጋራ ተጠቃሚነት ወሳኝ ናቸው።

በሞስኮ የተካሄደው የሩሲያ–አፍሪካ የኢኮኖሚና የሰብአዊነት ፎረምም ይህንኑ የጋራ ራዕይ ለማጠናከር የሚያግዝ መድረክ ሆኗል። በተለይ በተለያዩ የዓለም ኃይሎች መካከል የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተፅዕኖ እየተለዋወጠ ባለበት ዘመን፣ ሩሲያና አፍሪካ ከተለያዩ አጋሮች ጋር በጋራ ጥቅም፣ በእኩልነትና በአክብሮት ላይ የተመሠረተ ግንኙነት ለመገንባት ያላቸውን ፍላጎት የሚያሳይ ነው።

ይህ ሂደት ወደ ባለብዙ ዋልታዊ ዓለም ሽግግር በሚደረገው ውይይት ውስጥም የአፍሪካን ሚና ከፍ ለማድረግ የሚያስችል ዕድል ይፈጥራል።

የኢትዮጵያና ሩሲያ ወዳጅነት

በታሪክ፣ በባህልና በጋራ እሴቶች ከተገነባው የሩሲያ-አፍሪካ ግንኙነት መካከል 130 ዓመታት የሚጠጋው የሩሲያ-ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በጉልህ የሚጠቀስ ነው።
የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በታሪክ፣ በባህል፣ በሃይማኖትና በጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሠረተ ግንኙነት ነው።
የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ትስስር ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ባለፈ በሕዝቦቻቸው የነጻነት ፍላጎት፣ በብሔራዊ ማንነትና በባህላዊ እሴቶች ረገድ ጉልህ መመሳሰሎች አሉት።

ሩሲያ ሉዓላዊነቷን፣ ባህሏን፣ ታሪኳንና ሃይማኖታዊ ቅርሷን ለመጠበቅ በታሪኳ ያሳለፈችው ጉዞ አስደናቂ ነው። ኢትዮጵያም በራሷ ታሪክ ውስጥ ነጻነቷንና ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የከፈለችው መስዋዕትነት በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አለው።

በተለይ የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ኩራት ብቻ ሳይሆን፣ በአፍሪካና በዓለም ዙሪያ ለነጻነት የሚታገሉ ጥቁር ሕዝቦች የተስፋና የኩራት የታሪክ ክታብ ነው፡፡

በ1888 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1896) የአውሮፓ ኃያላን አፍሪካን በቅኝ ግዛት ለመቆጣጠር በተነሱበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ የጣሊያንን ወራሪ ጦር በአድዋ ጦርነት ድል በማድረግ ነጻነቷን አስጠብቃለች። ይህ ድል ለአፍሪካውያን የራስን እጣ ፈንታ በራስ የመወሰን አቅም ማሳያ ሆኗል።

ሩሲያም በታሪኳ እንደ 1812ቱ የናፖሊዮን ወረራና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚ ጀርመን ወረራ ያሉ ታላላቅ የውጭ ወረራዎችን በመመከት ሉዓላዊነቷን አስጠብቃለች። በተለይ በ1941–1945 በታላቁ የሀገር ፍቅር ጦርነት የሶቪየት ሕዝቦች የከፈሉት መስዋዕትነት በዓለም ታሪክ ከፍተኛ ቦታ ያለው ነው።

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከሀገሪቱ ታሪካዊና ባህላዊ ማንነት ጋር የተቆራኘች ተቋም ናት። በሩሲያ ሥነ ጽሑፍ፣ ሙዚቃ፣ ሥነ ሕንጻና ሥነ ጥበብ የተገነባው ሀብታም የባህል ቅርስም የሀገሪቱን ታሪካዊ ጥልቀት ያሳያል።

ክሬምሊን፣ የቅዱስ ባሲል ካቴድራልና በሴንት ፒተርስበርግ የሚገኙ ታሪካዊ ቤተ መንግሥታት የሩሲያን የሕንጻ ጥበብና ታሪካዊ ቅርስ የሚወክሉ ድንቅ ምሳሌዎች ናቸው።

የሁለቱ ሀገራት ታሪክ በተለያየ መንገድ ቢጓዝም፣ በሉዓላዊነት፣ በብሔራዊ ማንነትና በባህላዊ ቅርስ ጥበቃ ዙሪያ የሚታዩ የጋራ እሴቶች የሀገራቱን ወዳጅነት የሚያጠናክሩ ታሪካዊ መሠረቶች ናቸው።

“ነጻነት የሉዓላዊነትና የሰው ልጅ ህልውና መሠረት”- የአፍሪካ ጋዜጠኞች ድምፅ

በጉባኤው ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከመጡ ጋዜጠኞችና ተሳታፊዎች ጋር ባደረግኳቸው ውይይቶች አንድ የጋራ ሐሳብ በግልጽ ተንጸባርቋል፤ ነጻነት ለአንድ ሀገር የፖለቲካ መብት ብቻ ሳይሆን የህልውና፣ የክብርና የልማት መሠረት መሆኑ ከቦትስዋና የመጣው ጋዜጠኛ ጀስቲስ ካቫሄማቱኢ ነጻነት ለአንድ ሀገር የራሷን አቅጣጫ የመምረጥና በራሷ እጣ ፈንታ ላይ ውሳኔ የመስጠት መብት ማረጋገጥ እንደሆነ ይገልጻል። እንደ እሱ አባባል ነጻነት የሰው ልጅ ህልውና መሠረት ነው።

ከኡጋንዳ የመጣው ጋዜጠኛ ጆፍሪ ሴሩጎ በበኩሉ ነጻነት ለአንድ ሀገር እንደ ምግብና ውሃ መሠረታዊ ነገር መሆኑን ያነሳል። ከነጻነት ተነጥሎ መኖር ከባድ መሆኑን በመግለጽ፣ አፍሪካ ዘላቂ ልማትና እድገት ለማረጋገጥ ለችግሮቿ አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማበጀት እንዳለባት ያስገነዝባል።

ከጋና የመጣው ጋዜጠኛ ክሪስ ኮኔ ደግሞ ነጻነት የአንድ ሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ወሳኝ መሣሪያ መሆኑን ያብራራል። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ነጻነት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን በማንሳት፣ ጋና ከቅኝ ግዛት አገዛዝ ለመላቀቅ ያደረገችውን ትግልና ያስገኘችውን ታሪካዊ ትሩፋት ያብራራል።

ከጃኔት ሎላንድ ጋር ባደረግኩት ቃለ ምልልስ ደግሞ ነጻነትና ዴሞክራሲ ያላቸውን ጥልቅ ትስስር አንስታለች። ነጻነትን ማውራት ስለ ዴሞክራሲ ማውራት እንደሆነ የምታምነው ጃኔት፣ የአፍሪካ የዘመኑ ትግል የኢኮኖሚ ነጻነትን ማረጋገጥ መሆኑን ታስረዳለች።

እንደ እሷ አባባል የአፍሪካ መሪዎችና ዜጎች የሀገራቸው እጣ ፈንታ በሌሎች ሀገራት እጅ እንዳይወድቅ፣ በኢኮኖሚያዊ ራስን መቻልና በጋራ ትብብር ላይ በትጋት መሥራት አለባቸው። “ነጻነት ኃይል ነው፤ ነጻነትን ማጣት ደግሞ ኃይል አልባ መሆን ነው” ብላለች።

ከዛምቢያ የመጣው ጋዜጠኛ ጆሴፍ በበኩሉ ዛምቢያ ከብሪታንያ ቅኝ ግዛት ነጻ የወጣችበትን የነጻነት ታሪክ በማንሳት፣ ነጻነት በልማት፣ በራስ የመወሰን መብትና በብሔራዊ ክብር ላይ ያለውን አስፈላጊነት ያብራራል። ነጻነት ማለት በሌሎች ሀገራት ላይ ሳይደገፉ የራስን ውሳኔ በራስ መስጠት መቻል መሆኑንም ያስገነዝባል።

የጋዜጠኞቹ ሐሳቦች በአንድ ነጥብ ይገናኛሉ፤ ነጻነት የታሪክ ትውስታ ብቻ ሳይሆን የዛሬና የነገ የልማት፣ የኢኮኖሚ ነጻነትና የሉዓላዊነት መሠረት ነው በሚለው።

የሚዲያ ትብብርና የአፍሪካ የጋራ ድምፅ

በጉባኤው የታየው ትልቁ እድል የአፍሪካ ጋዜጠኞች እርስ በርስ የመተዋወቅ፣ የልምድ ልውውጥ የማድረግና የጋራ የሚዲያ ትብብርን የማጠናከር ዕድል ማግኘታቸው ነው።

ከኢትዮጵያ፤ ከቦትስዋና፣ ከኡጋንዳ፣ ከጋና፣ ከዛምቢያና ከሌሎች ሀገራት የመጡ ጋዜጠኞች ያነሷቸው ሐሳቦች አፍሪካ በተለያዩ የታሪክ ልምዶች ውስጥ ብታልፍም፣ በነጻነት፣ በልማት፣ በዴሞክራሲና በኢኮኖሚያዊ ራስን መቻል ረገድ የጋራ ጥያቄዎች እንዳሏት ነው።

የሚዲያው ሚናም እነዚህን የጋራ ጉዳዮች ለሕዝብ ማቅረብ፣ በሀገራት መካከል መግባባትን ማጠናከርና የተለያዩ አመለካከቶች በግልጽ እንዲቀርቡ መድረክ መፍጠር ነው። በዚህ ረገድ የሞስኮው ጉባኤ ለአፍሪካ ጋዜጠኞች የጋራ ውይይትን ከማሳደግ ባለፈ ወደፊት በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መሠረት የጣለ ሆኗል።

ከታሪካዊ ወዳጅነት ወደ ጋራ የወደፊት ግንባታ

በሞስኮ የተካሄደው 3ኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ የአፍሪካና የሩሲያ ግንኙነት ያለፈውን ታሪክ እያከበረ ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ ሊሸጋገር እንደሚችል ያመለከተ መድረክ ነው። በጉባኤው የተስተዋለው ደማቅ የሚዲያ ትብብር፣ የአፍሪካ ጋዜጠኞች የጋራ ተሳትፎና የተነሱት ሐሳቦች የዚህን ግንኙነት ሰፊ ትርጉም ያሳየ ነው።

ለኢትዮጵያ ደግሞ ከሩሲያ ጋር ያላት የረጅም ዘመን ታሪካዊ ግንኙነት የወዳጅነት ትውስታ ብቻ ሳይሆን፣ በትምህርት፣ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በኢኮኖሚና በባህል ልውውጥ የበለጠ የጋራ ጥቅም ለመፍጠር የሚያስችል እድል ነው።
የአድዋ ድልና የሩሲያ ታሪካዊ የሉዓላዊነት ትግሎች የሚያስታውሱን አንድ ትልቅ መርህ አለ፤ የሀገር ነጻነት፣ ማንነትና ክብር በታሪክ ብቻ የሚጠበቅ ብቻ ሳይሆን፤ በ የኢኮኖሚ አቅም፣ በእውቀት፣ በቴክኖሎጂና በጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት መሆኑን ነው፡፡

በሞስኮ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ጋዜጠኞችን ያገናኘው የሚዲያ ትብብር አንድ ጠቃሚ መልዕክት አስተላልፏል፤ አፍሪካውያን የጋራ ታሪካቸውን በጋራ ግንዛቤ ሲመለከቱ፤ የዛሬ ችግሮቻቸውን ሲተነትኑና የነገ ራዕያቸውን ሲቀርጹ ድምፃቸው የበለጠ ጠንካራ ይሆናል።

ሞስኮ ያሳየችውም ይህንኑ ነው፤ ታሪካዊ ወዳጅነትን ወደ ዘመናዊ ትብብር፣ የጋራ ውይይትን ወደ ጋራ ራዕይ እና የሚዲያ ተሳትፎን ወደ ጠንካራ የሕዝቦች ትስስር የማሳደግ እድል ነው።

በሰላማዊት ወንድወሰን ቱፋ
ከኤንቢሲ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን

Tags: EthiopiaFacebookMeta
ShareTweetShare
Previous Post

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድሯን እያካሄደች መሆኑ ተገለጸ

Next Post

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ትብብር ላይ የተሸረሸረውን እምነት መልሶ መገንባት ቀዳሚ ትኩረቷ ነው – ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ትብብር ላይ የተሸረሸረውን እምነት መልሶ መገንባት ቀዳሚ ትኩረቷ ነው – ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ትብብር ላይ የተሸረሸረውን እምነት መልሶ መገንባት ቀዳሚ ትኩረቷ ነው - ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)

የታሪክ፣ የሉዓላዊነትና የብሔራዊ ጥቅም ጥያቄ

የታሪክ፣ የሉዓላዊነትና የብሔራዊ ጥቅም ጥያቄ

የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቀናጀ ጥረት ማድረግ ይገባል

የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቀናጀ ጥረት ማድረግ ይገባል

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?