Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ሞስኮ፤ የታሪክ፣ የዲፕሎማሲና የወዳጅነት ጉዞ

ሞስኮ፤ የታሪክ፣ የዲፕሎማሲና የወዳጅነት ጉዞ

November 3, 2026
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

ከአዲስ አበባ እስከ ሩሲያ፤ በሦስተኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ የነበረኝ ቆይታ

ከጥቅምት 13 እስከ 21 ቀን 2019 ዓ.ም.

ሞስኮ ለእኔ የጉብኝት መዳረሻ ብቻ አልነበረችም፤ የታሪክ፣ የዲፕሎማሲ፣ የባህል፣ የጋዜጠኝነት ልምድና የአዳዲስ ወዳጅነት መገናኛ ሆና በሕይወቴ ውስጥ የማትረሳ ሥፍራ ይዛለች። በሦስተኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ ለመሳተፍ ያደረግሁት ጉዞ በሙያዊ ሕይወቴም ሆነ በግል ተሞክሮዬ የተለየ ትርጉም አለው።

ጥቅምት 13፤ ወደ ታሪካዊቷ ሩሲያ

የጉዞዬ መነሻ ቀን ከተለመደው የሥራ ቀን የተለየ ነበር። ከቀኑ 9፡00 ላይ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን ጋር የቃለ መጠይቅ ቀጠሮ ነበረኝ፤ በዚያው ምሽት 5፡35 ላይ ወደ ሞስኮ በረራ ስለነበረኝ የጉዞ ዝግጅቴን ከሥራዬ ጋር አጣምሬ አሳለፍኩ። ከሁለት የካሜራ ባልደረቦቼ ጋር 8፡30 ገደማ ከቢሮ ተነስተን ወደ ሩሲያ ኤምባሲ አቀናን። ከኤምባሲው የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ሊዎ ጋር ከተገናኘን በኋላ የቀረጻ ዝግጅታችንን አጠናቀቅን።

በቃለ መጠይቁ የሩሲያና የኢትዮጵያን ከ130 ዓመታት በላይ የዘለቀ የዲፕሎማሲና የወዳጅነት ግንኙነት ዳሰስን። ግንኙነቱ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በባህልና በሌሎች ዘርፎች ያስገኘውን ውጤት ተወያይተን፤ በተለይም ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ከሆነች ወዲህ በሁለቱ ሀገራት ትብብር የታዩ እድገቶችን አምባሳደሩ አብራሩ። ዋነኛው ትኩረታችን በጥቅምት 18 እና 19 የሚካሄደው ሦስተኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ ለኢትዮጵያ የሚኖረው ፋይዳ ነበር። ቃለ መጠይቁን ከጨረስን በኋላ አምባሳደሩንና ሊዎን አመስግኜ ወደ ቢሮ ተመለስኩ።
~

ወደ ቤት ተመልሼ ሻንጣዬን ካዘጋጀሁ በኋላ ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አመራሁ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ሞስኮ ቀጥታ በረራውን እ.ኤ.አ በታህሳስ 17 መጀመሩንና በሳምንት ስድስት ቀናት ወደ ዶሞዴዶቮ አየር ማረፊያ በረራ እንደሚያደርግ አውቃለሁ። ከምሽቱ 5፡35 ላይ በቦይንግ 787 አውሮፕላን ጉዞ ጀመርን። ስምንት ሰዓታት የፈጀው በረራችን ተጠናቆ ቅዳሜ ጠዋት 2፡05 ላይ ዶሞዴዶቮ ደረስን። የሞስኮ ቀዝቃዛ አየር የመጀመሪያ አቀባበል አደረገልኝ። የድንበር ፍተሻውን አጠናቀን ከወጣን በኋላ የጉባኤው አርማ የያዙ አስተባባሪዎች ተቀብለውን በተዘጋጀልን አውቶቡስ ወደ ፕሮስፔክት ሚራ በሚገኘው አዚሙት ሆቴል ወሰዱን። ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከመጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ተጓዝን፤ የጉዞውን ድካም በማረፍ አሳለፍኩ።

ጥቅምት 14፤ የሞስኮ የመጀመሪያ ልምምድ

ቀኑን በእረፍት ካሳለፍኩ በኋላ ምሽት ላይ ከሙያ አጋሮቼ ጋር የከተማዋን ድባብ ለመቃኘት ወጣን። የመጀመሪያው ያስደመመኝ የሞስኮ ሰላማዊና የተረጋጋ ከባቢ ነበር። ሰፊ ጎዳናዎቿ ላይ በቀዝቃዛው አየር፤ ወፍራም የክረምት ልብስ ለብሰው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች፣ ውሾቻቸውን ወይም ልጆቻቸውን ይዘው በእግር የሚጓዙ ነዋሪዎች ይታዩ የእግር ጉዞ ያደርጉ ነበር፡፡ ከተማዋ ትልቅና ዘመናዊ ብትሆንም ጸጥታዋናና የነዋሪዎቿ መረጋጋት በመጀመሪያው ምሽት ትኩረቴን ሳበ።

ጥቅምት 15፤ የታሪክና የባህል ውበት

እሁድ ጠዋት የሞስኮን ንጋት ከሆቴሌ መስኮት ተመለከትኩ። ቀዝቃዛው አየር ቢኖርም የጠዋቷ ፀሐይ ከተማዋን በለስላሳ ብርሃን አድምቃለች። ከቁርስ በኋላ ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር የጉብኝት ፕሮግራማችንን ተከትለን ወደ ክሬምሊን፣ ቀይ አደባባይና በተለያዩ ዘመናት የተገነቡ ጥንታዊ የሩሲያ አብያተ ክርስቲያናት ሄድን። በእያንዳንዱ ሥፍራ የሩሲያን ረጅም ታሪክ፣ የኪነ ሕንፃ ጥበብና የባህል ሀብት በተጨባጭ ለማየት ቻልን።

በጉብኝታችን ወቅት የሩሲያን ወታደራዊ ትርዒትም ተመለከትን። ከሰዓት በሩሲያ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የተዘጋጀ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ይዘት ያለው ትርዒትና መንፈሳዊ ዝማሬ ተመለከትን። በተለይ የዝማሬው ይዘትና አቀራረብ ጥልቅ ስሜት ፈጠረብኝ። ሩሲያ ባህሏን፣ ሃይማኖቷንና ታሪኳን ጠብቃ ለማቆየት የምታደርገውን ጥረት በተግባር የተመለከትኩበት፣ ለሀገር ፍቅርና ለታሪክ ክብር የሚሰጥ ቦታን ያስተዋልኩበት ቀን ነበር።

ጥቅምት 16፤ ከፕሬስ ሴንተር እስከ የሙያ ውይይት

በዚህ ቀን መዳረሻችን የጉባኤው ፕሬስ ሴንተር ነበር። ይህ ለጋዜጠኞች ወሳኝ የሥራ ማዕከል ሲሆን፤ ለሚዲያዎቻችን የምንልካቸውን ዜናዎችና ቪዲዮዎች የምናዘጋጅበት፣ በቀጥታ መግባት የማንችላቸውን ስብሰባዎች በስክሪን የምንከታተልበት ቦታ ነበር። የሥራ አፈጻጸሙን ገለጻ ከተቀበልን በኋላ ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ማክሲም ኦሬሽኪን ጋር ውይይት አደረግን። ከዚያ በኋላ ወደ ፕሬስ ሴንተሩ ተመልሼ የቪዲዮ መረጃዎችን አዘጋጅቼ ለኤንቢሲ ኢትዮጵያ ላክሁ። በዚያው ወቅት ከነዳጅ ላኪ ሀገራት ጉዳይ ጋር የተያያዙትን ጨምሮ በርካታ ተጓዳኝ ስብሰባዎች ይካሄዱ ነበር።

ምሽት ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከመጡ ጋዜጠኞች ጋር ተዋወቅሁ። ስለ ሀገሮቻችን፣ ስለ ሥራችንና ስለ ሙያዊ ተሞክሮዎቻችን ተወያይተን የወዳጅነት ግንኙነት ጀመርን።

ጥቅምት 17፤ ከማሪያ ዛካሮቫ ጋር ውይይትና የሞስኮ ሜትሮ

ይህ ቀን በጋዜጠኝነት ሥራዬ ልዩ ትዝታ ያስቀመጠ ቀን ነው። በፕሬስ ሴንተር ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ጋር ውይይት የማድረግ ዕድል አገኘሁ። በውይይቱ ወቅት ጋዜጠኞች በርካታ ጥያቄዎችን አቀረቡ። ዛካሮቫ በሩሲያና በአፍሪካ መካከል እየጠነከረ ስለመጣው አጋርነት፣ አፍሪካውያን ሉዓላዊነታቸውን በሚያከብርና በራሳቸው ውሳኔ ላይ በተመሠረተ ግንኙነት ለመጓዝ ስለሚያደርጉት ጥረት አብራሩ። አፍሪካ በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች አህጉር መሆኗን በማንሳት፣ ይህንን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ለዜጎቿ የተሻለ ኑሮ ማረጋገጥ የአፍሪካውያን ኃላፊነት መሆኑን አስገነዘቡ። ከውይይቱ የተረዳሁት ዋነኛ መልዕክት አፍሪካ የራሷን ሀብትና አቅም ለራሷ ጥቅም ማዋል እንዳለባት ነበር።

የቪዲዮና የጽሑፍ ዘገባዎቼን ለሚዲያዬ ከላክሁ በኋላ ከሙያ አጋሮቼ ጋር የሞስኮን ታዋቂ ሜትሮ ለመጎብኘት ወሰንን። ከጉባኤው አስተባባሪዎች አንዱ ኪሪል ሊያስጎበኘን አብሮን ሄደ። የሞስኮ ሜትሮ ታሪክ በግንቦት 1935 በተጀመረው የባቡር መስመር ይጀምራል። በጊዜ ሂደት እየተስፋፋና እየዘመነ የመጣው ሜትሮ በታሪኩ፣ በቴክኖሎጂው፣ በፍጥነቱና በተሳፋሪ አቅሙ የሚታወቅ ተቋም ሆኗል።

ከሁሉም በላይ ያስደመመኝ ከምድር በታች የተገነቡት የባቡር ጣቢያዎች ውበት ነበር። በጣቢያዎቹ ያሉ ሥዕላትች፣ ቅርጻ ቅርጾችና የኪነ ሕንፃ ጥበቦች የሩሲያን ታሪክና ባህል በግልጽ ይናገራሉ። በእነዚህ ጣቢያዎች መጓዝ ብቻውን የታሪክና የጥበብ ጉብኝት ያህል ነበር። ኪሪል ስለ ሜትሮው ታሪክና አሠራር ካብራራልን በኋላ በባቡር ወደ ሆቴላችን ተመለስን።

ጥቅምት 18፤ የሦስተኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ መክፈቻ

በጉጉት ስጠብቀው የነበረው ቀን ደረሰ። ጠዋት ወደ ፕሬስ ሴንተር አመራን፤ ስለ ጉባኤው የተለያዩ መረጃዎችን በቪዲዮ ቀርጬ ለሚዲያዬ ላክሁ። ከዚያም 48 የአፍሪካ ሀገራት ልዑካንና 22 የሀገር መሪዎች በተሳተፉበት ታላቅ መድረክ የተደረገውን ውይይት በእንግሊዝኛ ትርጉም ከፕሬስ ሴንተሩ ተከታተልኩ። ጉባኤው ያለፉትን ሰባት ዓመታት የፖሊሲ አፈጻጸም በመገምገም የ2027–2029 አዲስ የድርጊት መርሐ ግብር የሚያጸድቅበት ወሳኝ ምዕራፍ ነበር።

በዕለቱ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ያስተላለፉት መልዕክት ትኩረቴን ሳበ። “የአፍሪካ ዕጣ ፈንታ በጥቂት ኃያላን ሀገራት የሚወሰንበት ዘመን አብቅቷል” በማለት አህጉሪቱ በዓለም አቀፍ መድረክ የራሷን ውሳኔ የምታሳልፍበት ዘመን እየመጣ መሆኑን ገለጹ። አፍሪካን “የወደፊቱ አህጉር” ብለው በመጥራት፣ በፍጥነት እያደጉ ካሉ 20 ሀገራት መካከል 12ቱ በአፍሪካ እንደሚገኙ አመለከቱ። አንዳንድ ሀገራት ማዕቀብንና የኢኮኖሚ ጫናን በመጠቀም አፍሪካን ወደ ዕዳ ጥገኝነት ለመመለስ እየሞከሩ መሆኑን ጠቅሰው፣ አህጉሪቱ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር አማራጭ የክፍያ ሥርዓቶችን መጠቀም እንዳለባት አሳሰቡ። ንግግራቸውን ከተከታተልኩ በኋላ የዕለቱን ዘገባ አዘጋጅቼ ለኤንቢሲ ኢትዮጵያ ላክሁ።

ጥቅምት 19፤ የሩሲያ ታሪክና አቅም በኤግዚቢሽን

የጉባኤው ሁለተኛ ቀን መዳረሻችን በሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ ማዕቀፍ የተዘጋጀው የሩሲያን ታሪክ፣ ባህላዊ ሀብትና አቅም የሚያሳይ ኤግዚቢሽን ነበር። ከዋናው ኤግዚቢሽን ጎን ለጎን የተለያዩ ሁነቶችም ይካሄዱ ነበር። የኤግዚቢሽኑን ይዘትና የተለያዩ ሥፍራዎችን ከተመለከትኩ በኋላ ለሚዲያዬ የሚሆን የቪዲዮ ስታንድ አፕ አዘጋጀሁ።

የዘገባዬ ትኩረት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና በሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መካከል በተደረገው ውይይት ላይ ነበር። ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። በኒውክሊየር ኃይል፣ በጤናና በንግድ ዘርፎች ያለውን ትብብር፣ እንዲሁም በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሠረቱ የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን መወያየታቸውን በዘገባዬ ዳሰስኩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በሩሲያኛ ቋንቋ የተተረጎመውን “መደመር” መጽሐፋቸውን ለፕሬዝዳንት ፑቲን አበረከቱ።

በኤግዚቢሽን ላይ ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ቃለ መጠይቅ ያደረግሁላቸውን የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂንን አገኘሁ። ሰላምታ ከተለዋወጥንና ለጥቂት ጊዜ ከተወያየን በኋላ የጉባኤውን አስተባባሪ ኪሪልን አስተዋወቅኳቸው። የሥራዬን ድርሻ ከጨረስኩ በኋላ ከሙያ አጋሮቼና ከአዳዲስ ወዳጆቼ ጋር ወደ ሆቴላችን ተመለስን።

በአመሻሹ ፕሬዝዳንት ፑቲን ጉባኤው በጋራ መግለጫ መጠናቀቁን በጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ። በጋራ መግለጫው የኢነርጂ ሉዓላዊነትና ደህንነትን ማረጋገጥ፣ ወረርሽኞችንና ተላላፊ በሽታዎችን ለመዋጋት ዝግጁነትን ማጠናከር፣ የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ሥርዓቶችን ከፖለቲካ ተፅዕኖ መጠበቅ፣ ታሪክን የማዛባትና ባዕድ ትርክቶችን የመጫን ሙከራዎችን መታገል እንዲሁም በዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ ማሻሻያ ማድረግ ተካተው ነበር።

በተጨማሪም የተመድ የፀጥታ ምክር ቤትን አሁን ያለውን የጂኦፖለቲካዊ እውነታ በሚያንጸባርቅ መልኩ ማሻሻል፣ ያለበቂ ምክንያት የሲቪል መርከቦችን ማገድና መያዝን ማውገዝ፣ በቅኝ ግዛት ወቅት ለደረሱ ጉዳቶች ግምገማና ካሳ የሚያስችሉ የሕግ ማዕቀፎችን መዘርጋት፣ በጋራ ንግድ የአገር ውስጥ ገንዘቦችን አጠቃቀም ማስፋፋት፣ የሽብርተኝነት መከላከል ትብብርን ማጠናከርና “ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” በሚለው መርህ ግጭቶችን መፍታት የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ተካትተው ነበር።

ጥቅምት 20፤ የስንብት ዕለት

ወደ አዲስ አበባ የምንመለስበት ቀን ደረሰ። ጠዋት ከቁርስ በኋላ ከሙያ አጋሮቼና ከጓደኞቼ ጋር ወደ ዱብሮቭካ ገበያ ለመሄድ ሜትሮ ተሳፈርን። ገበያውን በደንብ እንዲያሳየን ሮቤል የተባለ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወዳጃችን ተቀላቀለን። በገበያው ጫማ፣ ልብስ፣ ሽቶና ሌሎች ዕቃዎችን ገዛን፤ የመመለሻ በረራችን ሰዓት እየተቃረበ ስለነበር ግዢያችንን በፍጥነት አጠናቀቅን። በሜትሮ ወደ አዚሙት ሆቴል ተመልሰን ምሳ ከበላን በኋላ ዕቃዎቻችንን ሰብስበን በቆይታችን ያፈራናቸውን ወዳጆች ተሰናበትን። ከዚያም ወደ ዶሞዴዶቮ አየር ማረፊያ አመራን።

የማይረሱ የሞስኮ ትዝታዎች

በሞስኮ ያሳለፍኩት ጊዜ በጥሩ ልምድ፣ በአዳዲስ እውቀት፣ በሰፋ የዓለም እይታና በወዳጅነት የተሞላ ነበር። የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ኢቫ፣ ዳርያና ኪሪል በትህትናቸው፣ በቅርበታቸውና በአቀባበላቸው በልቤ ውስጥ የተለየ ቦታ ይዘዋል። ከተዋወኳቸው የአፍሪካ ጋዜጠኞች መካከል የቦትስዋናው ጀስቲስ፣ የታንዛኒያዋ ጃኔት፣ የኡጋንዳው ጂኦፍሪ፣ የዛምቢያው ጆሴፍና ሌሎችም አዳዲስ ወዳጆቼ ሆነዋል።

የሞስኮ ቆይታዬን ሳስታውስ በመጀመሪያ የሚታወሰኝ አጥንት ድረስ የሚዘልቀው ቅዝቃዜዋ ነው። ከዚያ በኋላ ኮስታራ ቢመስልም ሲቀርቡት ሞቅ ያለ ወዳጅነት የሚያሳየው የሩሲያ ሰው፣ ውብ አብያተ ክርስቲያናት፣ የኪነ ሕንፃ ጥበብ የተላበሱ ሕንፃዎችና በሩሲያ ማዕድ ላይ በብዛት የሚቀርበው ድንች ይታወሱኛል። ከሁሉም በላይ ግን በዚህ ጉዞ ያገኘኋቸው ወዳጆች፣ የተማርኳቸው ታሪኮችና ያየኋቸው ባህሎች በማስታወሻዬ ውስጥ ልዩ ሥፍራ ይዘዋል።

በዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ ሁነት በክብር በመሳተፌ የክብር ሰርተፊኬት ተሸልሜያለሁ። ሰርተፊኬቱን ከሩሲያ ፕሬዝዳንት አማካሪ ከአንቶን ኮብያኮቭ መቀበሌ ለእኔ ትልቅ ክብርና ደስታ ፈጥሮልኛል።


ጥቅምት 20–21፤ ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ- ወደ ቤት መመለስ

በጥቅምት 20 ቀን ከምሽቱ 3፡30 ገደማ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767 አውሮፕላን ወደ አዲስ አበባ የመመለሻ ጉዞአችንን ጀመርን። በጥቅምት 21 ቀን ጠዋት 11፡30 ገደማ በሰላም አዲስ አበባ አረፍን። አካሌ ከሞስኮ ቢመለስም በአእምሮዬና በልቤ የታተመው ትዝታ ግን አብሮኝ ቀጥሏል። ከጉዞዬ ያገኘሁት ልምድ የጋዜጠኝነት እይታዬን አስፍቷል፤ የተገናኘኋቸው ሰዎችም በዓለም ላይ የወዳጅነት ድልድይ እንዳለ አስተምረውኛል። ሞስኮ ለእኔ የጉብኝት ከተማ ብቻ አይደለችም፤ ትምህርት ቤቴ፣ የታሪክ መዝገቤ፣ የወዳጅነት መነሻዬና የማይረሳ የሕይወት ተሞክሮዬ ናት።                      

የጉዞ ማስታወሻ በሰላማዊት ወንድወሰን ቱፋ

Source: @NBCEthiopia
Via: NBC Ethiopia
Tags: #addisababaEthiopiaFacebookMetaRussiaRussia Africa summit
ShareTweetShare
Previous Post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋዜጣዊ መግለጫ

Next Post

MOSCOW: A Journey Through History, Diplomacy and FriendshipFrom Addis Ababa to Russia: My Experience at the Third Russia–Africa Summit

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ሞስኮ፤ የታሪክ፣ የዲፕሎማሲና የወዳጅነት ጉዞ

MOSCOW: A Journey Through History, Diplomacy and FriendshipFrom Addis Ababa to Russia: My Experience at the Third Russia–Africa Summit

ከሰሜን እዝ ጥቁር ሌሊት እስከ ታሪካዊ ድል !

ከሰሜን እዝ ጥቁር ሌሊት እስከ ታሪካዊ ድል !

ኤቨረስት ተራራ አቅራቢያ ሁለት ሄሊኮፕተሮች ተጋጩ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?