NBC Ethiopia
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ማይክል ኦዌን ለእንግሊዙ “4-4- 2″ መጽሔት እንደተናገረው፣ በ2001 ‘ባሎን ዶር” ን ሲያሸንፍ፣ ብዙውን ጊዜ ከዚህ ሽልማት ጋር አብሮ የሚመጣውን ያህል እውቅና አላገኘም።
ሃሪ ኬን ይህንን ሽልማት እስኪያሸንፍ ድረስ፣ ‘ባሎን ዶር’ን ያሸነፈ የመጨረሻው እንግሊዛዊ ተጫዋች ኦዌን ነበር።
ኦዌን ‘ባሎን ዲ ኦር’ን ያሸነፈው በ22 ዓመቱ ሲሆን፣ ይህ የሆነው ከሊቨርፑል ጋር አስደናቂ የውድድር ዘመን ካሳለፈ በኋላ ነበር፤ በዚያም ወቅት ክለቡ ሦስት ዋንጫዎችን (ሊግ ካፕ፣ ዩኤፋ ካፕ እና ኤፍኤ ካፕ) አሸንፎ ነበር።
እ.ኤ.አ. በ2001፣ ኦዌን እንግሊዝ ጀርመንን 5 ለ 1 በረታችበት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ ሦስት ግቦችን አስቆጥሮ ሃትትሪክ መስራት ችሎ ነበር። በሙኒክ የተካሄደው ይህ ጨዋታ፣ የእንግሊዝ እጅግ አደገኛ አስፈሪው የፊት መስመር ተጫዋዦች መሆኑንም ያረጋገጠበት ነበር።
በእግር ኳስ ዓለም ከፍተኛውን የግል ክብር ለማግኘት፣ ኦዌን እንደ ዚነዲን ዚዳን፣ ቲየሪ ሄንሪ፣ ራውል፣ ሪቫልዶ፣ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አጋሩ ዴቪድ ቤካም እና ሉዊስ ፊጎ ያሉ ኮከብ ተጫዋቾችን መርታት ግድ ብሎት ነበር።
ኦዌን ፡- “‘ባሎን ዶር’ን ባሸነፍኩበት ወቅት፣ ሊሰጠኝ የሚገባውን ያህል እውቅና ያገኘሁ አይመስለኝም። በእኛ ሀገር፣ ‘ባሎን ዲ ኦር’ ያን ያህል ትልቅ ቦታ አልነበረውም። በስፔን በነበርኩበት ጊዜ ግን፣ ይህንን ሽልማት በማሸነፌ እንደ ጀግና ይቆጥሩኝ ነበር። ይህንን ክብር በማግኘቴ በጣም እኮራለሁ።”
“የአሸናፊዎችን ዝርዝር ወደ ኋላ መለስ ብዬ እመለከታለሁ፤ አሁንም በስልኬ ላይ አስቀምጬዋለሁ። በዝርዝሩ ውስጥ ማን ሁለተኛ፣ ሦስተኛ፣ አራተኛ እና የመሳሰሉትን ደረጃዎች እንደያዘ የሚያሳይ የነጥብ ሰንጠረዥ ምስል አለ።”
“ያንን ዝርዝር ስትመለከት፣ በእውነት አስደናቂ ነው። በልጅነቴ ሁሌም የማልመው የነበረው ይህንኑ ነበር። እግር ኳስ ተጫዋች መሆን ብቻ ሳይሆን፣ ምርጡ እግር ኳስ ተጫዋች መሆን እፈልግ ነበር። አሁን ወደ ኋላ መለስ ብዬ ሳስበው፣ ‘ባሎን ዶር’ን ማሸነፌን፣ እየተጫወትኩ በነበረበት ጊዜ ከነበረው የበለጠ አደንቀዋለሁ። በወቅቱ ገና 22 ዓመቴ ስለነበር፣ እንደማንኛውም ሌላ ዋንጫ ብቻ ነበር የሚሰማኝ፤ በዚያን ጊዜም የማስበው እንደገና እንዴት እንደማሸንፈው ብቻ ነበር።”
ኦዌን ሽልማቱን ሲያሸንፍ፣ ‘ባሎን ዶር’ በክርስቲያኖ ሮናልዶ እና በሊዮኔል ሜሲ ዘመን እንደነበረው ከፍተኛ ዝና እና ተቀባይነት ገና አላገኘም ነበር። ከ2000ዎቹ መጨረሻ አንስቶ እስከ 2010ዎቹ ድረስ፣ ሁለቱ ተጫዋቾች በየወቅቱ ማለት ይቻላል ለዚህ ሽልማት ይፎካከሩ ነበር፤ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የእግር ኳስ አፍቃሪዎችም የዓለማችን ምርጥ ተጫዋች ለመሆን ያደረጉትን ይህንኑ ፉክክር ይከታተሉት ነበር።
እስከ ዛሬ ድረስ፣ በሊቨርፑል ክለብ ውስጥ እያለ ‘ባሎን ዶር’ን ያሸነፈ የመጨረሻው የሊቨርፑል ተጫዋች ኦዌን ነው።
በ-ሳምሶን አበበ
። ። ።
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ
https://linktr.ee/NBCEthiopiaTV
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት
#Ethiopia












