የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞዛምቢክ ናካላ ከተማ አዲስ በረራ መጀመሩን አስታወቀ።
ናካላ ከተማ ለአየር መንገዱ ከማፑቶ እና ቤይራ ቀጥሎ በሞዛምቢክ ሦስተኛው መዳረሻው ሆናለች።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዘሪሁን አበበ፣ በኢትዮጵያ የሞዛምቢክ አምባሳደር ኑኖ ቶማስ እና የአየር መንገዱ የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ ረታ መላኩ ተገኝተዋል።
አዲሱ የበረራ መስመር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዲሁም ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝምን በማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።




Source:
@NBCETHIOPIA
Via:
@NBCETHIOPIA












