
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ወጣቱ ከጦርነት ይልቅ ወደ ልማት እንዲመለስ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስተሩ በመልእክታቸው፣ ወጣቶች ለጦርነት ማብረጃ ከመሆን ወጥተው፣ የራሳቸውንና የማህበረሰቡን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚገነቡ መሆን አለባቸው ብለዋል ።
በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ ላሉ የትግራይ ወጣቶች ጥሪያቸውን ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ከጦርነት እሳቤ እንዲወጡ፣ ሰላማዊ አማራጮችን እንዲከተሉ እና በአካባቢያቸው የልማት ግንባታላይ የቡኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበክቱ አሳስበዋል::
በብዙ ስቃይና እንግልት ውስጥ የቆዩ እናቶች ከልጆቻቸው ጋር መገኘት አለባቸው፡፡ ያጣነውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት እናድስ፡፡ መሰረተ ልማቶችን ዳግም እንገነባለን” ነው ያሉት፡፡
በቅርቡ የትግራይ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው እንዲመለሱ የሚያስችል የትጥቅ መፍታት መርሀግብር በመቀሌ ከተማና አካባቢዋ እየተከናወነ መሆኑን አስታውሰው፣ በመሆኑም ወጣቶች ከተሳሳተ የጦርነት ግፊት መልቀቅና በሰላም ወደ ህዝብ በመቀላቀል የልማት ስራ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።
በ ታደለ ገበየሁ












