NBC Ethiopia

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሕንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራማኒያም ጃይ ሻንካር (ዶ/ር) ጋር በጽሕፈት ቤታቸው በሁለትዮሸ እና በወቅታዊ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሚኒስትሮቹ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በትምህርት እና ባህል፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በዲጂታይዜሽን ዙሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማስፋት እና ለማጠናከር መክረዋል።
የሕንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቅርቡ በሕንድ አስተናጋጅት በተካሄደው የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ ኢትዮጵያ ለነበራት ውጤታማ ተሳትፎ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Source:
@NBCETHIOPIA
Via:
@NBCETHIOPIA












