NBC Ethiopia
የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጠላቶች ተልዕኮ ተሸክሞ ውጊያ የጀመረው ፀረ-ህዝብ ቡድን ሴራው በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ብቃትና ውጤታማነት ከሽፏል ሲሉ ከኤን ቢሲ ኢትዮጵያ ጊዜ ግስ ፕሮግራም ጋር ቆይታ ያደረጉት የቀድሞ የኢፌዲሪ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ተናገሩ። ህዝባዊ መሰረትና አላማ የሌለው የወንጀለኞች ቡድን ብለው የጠቀሱት ስብስብ የጀመረው ውጊያ ከመቀልበሱም በላይ በመሰረታዊነት በሽንፈት አብቅቷል ማለት ይቻላል ብለዋል ጄኔራሉ
በአሁኑ ሰዓት ህውሃት የሚባል አካል የለም፣ የወንጀለኞች ስብስብ ቡድን ነው፤ ትግራይን ሲያምስ የቆየው ያሉት ጄኔራሉ በተለያዩ ወንጀል ተሰማርተው የነበሩ አካላት ከተጠያቂነት ለመሸሽ እና የባዕዳን ሃገራትን ተልእኮ ለማሳካት የተነሱ ናቸው ብለዋል።
ከትግራይ ህዝብ ፍላጎት በተቃራኒ ቆመው ህዝቡን ሰላም ለመንሳት ቢቻላቸው ሀገር ለመበታተን የጀመሩት ውጊያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሽንፈታቸውን አረጋግጧል ያሉት ጄኔራሉ፤ ህዝቡ ልጆቹን እንዲሰበስብ እንዲሁም አላማ የሌለው ጦርነት ውስጥ የሚሳተፉ ወጣቶችም ወደ ቤት እንዲመለሱ እና በእብደት ጦርነቱን የጀመሩ አካላትም እጃቸውን እንዲሰጡ ጄኔራሉ ጥሪ አቅርበዋል::












