
ለ2026 የዓለም ምርጥ አትሌት ሽልማት እጩዎች ህዳር 29 ቀን በሞናኮ ከሚካሄደው የዓለም የአትሌቲክስ ሽልማቶች በፊት ይፋ ሆነዋል።
በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ባለሙያዎች ቡድን የተመረጡት እጩዎች 10 የሴቶች የዓለም ምርጥ አትሌት እና 10 የወንዶች የዓለም ምርጥ አትሌት ያካትታሉ።
ለስፖርቱ ሌላ አስደናቂ ዓመት በሆነው በዚህ ዓመት፣ እጩዎቹ በዓመቱ ውስጥ በተካሄዱት የመጀመሪያ የዓለም አትሌቲክስ ኡልቲማ ሻምፒዮና እና በዓለም አትሌቲክስ ተከታታይ ዝግጅቶች እንዲሁም በዓለም ዙሪያ በተለያዩ የአንድ ቀን ውድድሮች ፣ የሌብል የጎዳና ውድድሮች እና ሌሎች ዝግጅቶች ላይ የተገኙ አንዳንድ አስደናቂ ውጤቶችን ያንፀባርቃሉ።
ለ2026 የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት ሽልማት ከታጩ አትሌቶች መካከል ትግስት አሰፋ ከኢትዮጵያ የበርሊን ማራቶንን በ2:11:04 እንዲሁም የለንደን ማራቶንን በ2:15:41 ሰዓት በማሸነፍ ለሴቶች ብቻ በተደረገ ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን በማስመዝገብ በእጩ ውስጥ ተካታለች።
ሳምሶን አበበ












