Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት

October 2, 2026
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

“ኢሬቻ ሰላም ነው! ገዳ ስልጣኔ ነው! የኢትዮጵያ ስልጣኔ አይቀሬ ነው!

እንኳን የክረምቱን አስቸጋሪ ወቅት በሰላም አሳልፋችሁ ለብሩሁ ብራ አደረሳችሁ። የክረምቱ ጨለማ አልፎ የብራዋ ጀንበር ስትወጣ ኦሮሞ በአንድነት ወጥቶ በባህሉ ስርዓት ወደ መልካ ይሄድና የክረምቱን ጨለማ ያሳለፈውን ፈጣሪውን ያመሰግናል። ለሚመጣውም ጊዜ ተስፋን ይሰንቃል። አባቶች “ማሬሆ” እናቶች ደግሞ “አራሮ” በማለት ለቸሩ አምላክ ምስጋና ያቀርባሉ። ወደ መልካው በመውረድም የምስጋና ስርዓቱን ያስጀምራሉ።

የክረምቱ ጨለማ በርካታ የማይመቹ ነገሮች አሉት። የሰውንና የእንስሳትን እንቅስቃሴ በመገደብ ያሰቡበት እንዳይደርሱ ያደርጋል። የክረምቱ ዶፍ ዝናብ፣ ጎርፉ፣ ጭቃውና አንሸራታቹ ድጥ ብራን በእጅጉ ተናፋቂ ያደርጋል። ለዘመናት የቆየው አብዛኛው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት፣ የፖለቲካ ባህርይና አስተዳደርን ከክረምቱ አስቸጋሪ ወቅት ጋር ማመሳሰል እንችላለን።

ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ሆና ሳለች የስሟን ያክል መሆን ሳትችል ቆይታለች። በርካታ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሀብቶች እያሏት በዕውቀትና በስርዓት ስላልተመራ ብቻ ወደ ተጨባጭ አቅም መቀየር ባለመቻሏ የድህነት ተምሳሌነት ሆና ስትጠቀስ ኖራለች። የረጅም ዘመናት ሀገረ መንግስትነት ቢኖራትም የህዝብን ችግር የሚፈታና ሀገርን የሚያሻግር ዘመናዊ አስተዳደር ለመገንባት ግን ስትቸገር ቆይታለች። ከራሷ አልፎ አለም አቀፍ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችል መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ቢኖራትም አልተጠቀመችበትም። ከዚህ የተነሳ በእህል ጎተራ ላይ ተቀምጣ የምትራብ፣ ውሃ እያላት የምትጠማና እያለዉ ያጣ ህዝብ ሆነን ኖረናል።

የክረምቱ ጨለማ ማለፉ የተፈጥሮ ህግ ነው።

የክረምቱ ዝናብ ሲያልፍ በጎ ነገርም ትቶ ይሄዳል። የዝናቡ ውሃ መሬት ውስጥ ዘልቆ አፈሩን አርሶ አዝርዕት ያበቅላል፤ የተዘራውን ዘር አብቅሎ እንዲያፈራ ያደርጋል፤ የብራውን አበባ አፍክቶ ተስፋን ያለመልማል። የብራው አበባ መዓዛው ያውዳል፤ ቀለሙም ይማርካል፤ የተዘራው ሰብልም በብራ ወቅት ፍሬው ይሞላል፤ ለዚህ ነው ኦሮሞ ለብራ ትልቅ ስፍራ ያለው።

ህዝባችን በትግሉ ያመጣው ለውጥም ከብራ ጋር ይመሳሰላል። ለኢትዮጵያ የሰነቅነው የብራ ራዕይ፡ ጠንካራ አንድነት ላይ የተመሠረተች ፣ ሉዓላዊነቷ የተከበረ፣ በስፋት የምታመርትና ማንኛውንም ዓይነት ፈተና የምትቋቋም ለአፍሪካ ግንባር ቀደም ተምሳሌት የሆነ ሀገር መገንባት ነው። ኢትዮጵያን ወደ ስልጣኔ የማሻገር ስትራቴጂያዊ እቅድ በተግባር ላይ እየዋለ ነው። በእቅዱ መሠረትም የለውጡ መንግስት የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮችን ወደ ዕድል እየቀየረ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካው መስክ ታላላቅ ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ፣ ሀገራዊ ምክክር በተሳካ ሁኔታ መከናወኑ፣ እንደ ማዳበሪያ ፋብሪካና የነዳጅ ፕሮጀክቶች እንዲሁም የቢሾፍቱ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መጀመራቸው የስልጣኔ ጀንበር ለኢትዮጵያ ብቅ እያለች ለመሆኗ ጥቂት ማሳያዎች ናቸው።

የኦሮሞ ህዝብ ቋንቋውን፣ ባህሉንና እሴቱን ለማሳደግ ያነሣውን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ለመመለስ በባህል ልማት ረገድ የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ ወደ መልካው ተመልሶ ስርዓት ውስጥ መግባቱ፤ የሆራ ሀርሰዴ ኢሬቻ ደግሞ በቢሾፍቱ ውብት ደምቆ ከፍ ብሎ መከበሩ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው።

አሁን የምንገነባው ስልጣኔ በጥንታዊ እሴቶቻችን ላይ የተመሠረተ እንዲሆን በመደመር ፍልስፍና አቅደን ለጋራ እውቀት፣ የገዳና የሰፉ ትምህርት፣ ለጋራ ፍትህ ባህላዊ ሸንጎዎችን አቋቁመን፣ ለጋራ ልማት የዜግነት አገልግሎትን ዘርግተን፣ ለጋራ ደህንነት ደግሞ የስርዓቱን ጠባቂዎች አደራጅተን ስርዓት እየገነባን እንገኛለን።

ለኢትዮጵያ መውጣት የጀመረው ይህ የለውጥ ብርሃን በየትኛውም የክረምት ጨለማ፣ ዶፍና ጭቃ ተንሸራትቶ ሊደናቀፍ አይችልም። ፈተናዎች ግን አሁንም ይኖራሉ። እነዚህ ፈተናዎች ግን ከኢትዮጵያና ህዝቦቿ አቅም በታች ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን አንድነቱን አጠናክሮ፣ ወንድማማችነትን አስፋፍቶ በፍቅር በመደመር የኢትዮጵያን ስልጣኔ እውን ለማድረግ እየተባበረ ይገኛል። እኛም በህዝብ ድምፅ እንደተመረጠ መንግስት ከእሴታችን በፈለቀው የመደመር እሳቤ ላይ ተመስርተን የኢትዮጵያን ስልጣኔ ዕውን ለማድረግ ተግተን በመስራት ላይ እንገኛለን።

የአድዋ አባቶቻችንን ጀግንነት በማስቀጠል ኢትዮጵያን ከጠላት እየጠበቅን ነን። እነርሱ ባሰመሩልን ድንበር ውስጥ እኩልነት፣ ሰላምና ብልፅግና እንዲረጋገጥ በፅናት እየሠራን እንገኛለን። የገዳ ስርዓት እሴትን መነሻ በማድረግ የሀሳብ ልዩነትን በመደማመጥ ለማስተካከል ሀገራዊ ውይይት አድርገናል።

በሌላ በኩል ደግሞ “እኔ ስጋ ብቻ ልብላ፤ እንስሳዬ ግን እንዳይነካ” የሚል ጠላትና ባንዳ ፊት ቆመን የሀገራችንን ጥቅም እናስከብራለን። መንገድ ስተው ከሀገራቸው በተቃራኒ ለቆሙ ወንድሞቻችን ያለን መልእክት ኦሮሞ ‘ከሚያመሹበት የሚያድሩበት ቤት ይሻላል’ ብሎ እንደሚተርት አሁንም ፊታቸውን ወደ ሰላም ከመለሱ፤ የሰላም በር እንደተከፈተ ያለ መሆኑን ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ።

ኦሮሞ በትግሉ ነፃ ወጥቷል። ከዚህ በኋላ በጠብመንጃ አፈሙዝና ከጠላት ጋራ በመወገን የሚመለስ የኦሮሞ ጥያቄ ፈፅሞ አይኖርም።

የተከበርከው ህዝባችን ሆይ፣

የኢሬቻን በዓል ስናከብር እንደ እሴቱ አንድነትን አጥብቀን፣ እጃችንን ለሰላምና ለዕርቅ ዘርግተን፣ ቀልባችንን ወደ ይቅርታ መልሰን ስላገኘነው ነገር ፈጣሪን እያመሰገንንና እየተንከባከብን ያጣነውን ደግሞ በትዕግስት በመጠበቅ፤ ልክ ትናንት ኦሮሞ በአባቶቹ ደምና አጥንት ኢትዮጵያን እንደገነባ፣ ዛሬም የኢትዮጵያን ስልጣኔ ዕውን ለማድረግ ባለን ዕውቀት፣ አቅምና ሀብት ሁሉ ከሌሎች ወንድም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመሆን በግንባር ቀደምነት ኢትዮጵያን እንድናፀና ጥሪዬን አቀርባለሁ!

ኢሬቻ ሰላም ነው! ገዳ ስልጣኔ ነው! የኢትዮጵያ ስልጣኔ አይቀሬ ነው!

ከለቻና ጫጩው የሰላም ይሁን!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

መስከረም፣ 2019 ዓ.ም.

Tags: #irreechaEthiopiaPM Abiy Ahmed
ShareTweetShare
Previous Post

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ አብዱላሂ አደንን የአስተዳደሩ ከንቲባ  አድርጎ ሾመ

Next Post

የኢትዮጵያና አርሜኒያ የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ወደ ላቀ የንግድና ኢንቨስትመንት የኢኮኖሚ አጋርነት እየተሸጋገረ ነው – አምባሳደር ሳሀክ ሳርጊሲያን

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የኢትዮጵያና አርሜኒያ የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ወደ ላቀ የንግድና ኢንቨስትመንት የኢኮኖሚ አጋርነት እየተሸጋገረ ነው – አምባሳደር ሳሀክ ሳርጊሲያን

የኢትዮጵያና አርሜኒያ የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ወደ ላቀ የንግድና ኢንቨስትመንት የኢኮኖሚ አጋርነት እየተሸጋገረ ነው - አምባሳደር ሳሀክ ሳርጊሲያን

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

የኢትዮጵያና አርሜኒያ የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ወደ ላቀ የንግድና ኢንቨስትመንት የኢኮኖሚ አጋርነት እየተሸጋገረ ነው – አምባሳደር ሳሀክ ሳርጊሲያን

የኢትዮጵያና አርሜኒያ የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ወደ ላቀ የንግድና ኢንቨስትመንት የኢኮኖሚ አጋርነት እየተሸጋገረ ነው - አምባሳደር ሳሀክ ሳርጊሲያን

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?