
የአማራ ክልል ምክር ቤት አቶ አረጋ ከበደን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾመ
የአማራ ክልል ምክር ቤት አቶ አረጋ ከበደን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።
የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን መሥራች ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ፈታኝ የጸጥታ ችግር በገጠመው ወቅት ኃላፊነት ወስደው ክልሉ እንዲረጋጋ ያደረጉ ብርቱ መሪ መሆናቸው ተገልጿል።
በዚህም ክልሉን በብቃት በመምራት ወደ ሰላምና ልማት መመለስ የቻሉ መሆናቸውም በምክር ቤቱ ተነስቷል።
ምክር ቤቱም አቶ አረጋ ከበደን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ኡመርን በድጋሚ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾመ
የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 7ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት የመጀመሪያ ጉባኤ አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ኡመርን በድጋሚ ርዕሰ መስተዳድር በማድረግ ሾሟል።
የሶማሌ ክልል ምክር ቤት እንዲሁም ኢብራሂም ኡስማንን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በማድረግ ሰይሟል።
የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 7ተኛው የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
መሳይ ሀይሉ (ዶ/ር) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መሳይ ሀይሉን (ዶ/ር) የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾመ።
የክልሉ ምክር ቤት መስራች ጉባዔ በሀዋሳ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህም መሳይ ሀይሉ (ዶ/ር) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል።
መሳይ ሀይሉ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል።
ዶክተር መሳይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕረዝደንትነት ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች የሥራ ሃላፊ ሆነው በውጤታማነት ማገልገላቸው አንስተዋል።
በዚህም ምክር ቤቱ መሳይ ሀይሉ (ዶ/ር) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።
ምክር ቤቱ በመሥራች ጉባኤው የክልሉን ምክትል ርእሰ መሥተዳድር እና ሌሎች ሹመቶችንም እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።










