Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Politics

የኢትዮጵያ እና ኬንያ ግንኙነት – የፓን አፍሪካኒዝም ህያው ማሳያ

የኢትዮጵያ እና ኬንያ ግንኙነት - የፓን አፍሪካኒዝም ህያው ማሳያ

September 30, 2026
in Politics
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

የኢትዮጵያና የኬንያ ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ከታሪካዊው የድንበር ስምምነት ጀምሮ እስከ አሁን በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ በታሪካዊ ወዳጅነትና በጋራ ተጠቃሚነት ማዕቀፍ ውስጥ ከሚጠቀሱ የዲፕሎማሲ ትብብሮች መከካል አንዱ ነው።

የሁለቱ አገራት ግንኙነት ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በየዘመናቱም የመሪዎችና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነታቸው ባልተቋረጠ መልኩ የቀጠለ ነው።

ይህ ታሪካዊ መስተጋብር በፓን አፍሪካኒዝም መርሆዎች ላይ ተመስርቶ ካደገ በኋላ፣ ኬንያ ነፃነቷን ባወጀች ማግስት እ.አ.አ ጁን 26/ 1964 የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመከፈት በይፋ ተመሠረተ።

ይህም በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ውስጥ ለዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ አስተማማኝ አጋርነት ለመፍጠር የመጀመሪያውን መሠረት ጥሏል።

የኢትዮጵያና የኬንያ ሁለንተናዊ ግንኙነት በመከባበርና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ብቻ ሳይሆን፣ የአህጉሪቱን ነፃነትና አንድነት ከፍ ለማድረግ ጽኑ መሠረት የጣለ የፓን-አፍሪካኒዝም ህያው ተምሳሌት ነው።

ኢትዮጵያና ኬንያ ቅኝ ግዛትን በመታገልና ለአፍሪካ ነፃነት መሠረት በመጣል ረገድ የነበራቸው ታሪካዊ ሚና የሁለቱን አገራት ወዳጅነት በጽናት አስተሳስሯል።

የሁለቱ አገራት መሪ የነበሩት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ እና ጆሞ ኬንያታ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ አፍሪካ ኅብረት) መመስረት የነበራቸው ግንባር ቀደም ሚና፣ ዛሬ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና በፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ዘመን ወደ ላቀ የኢኮኖሚና የመሠረተ ልማት ትስስር ተሸጋግሮ “የአፍሪካውያን መፍትሔ ለአፍሪካ ችግሮች” የሚለውን መርህ በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።

ይህ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ባለፉት አሥርት ዓመታት በዘርፈ-ብዙ የትብብር መስኮች ወደ ላቀ ምዕራፍ ተሸጋግሯል።

ሁለቱ አገራት በሰላም፣ በጸጥታና በደህንነት ረገድ እጅግ የጠበቀ ቁርጠኝነት ያላቸው ሲሆን፣ በተለይም ሽብርተኝነትን (አል-ሸባብን) ለመዋጋት፣ የድንበር አካባቢዎችን ለማረጋጋት እና የጋራ መረጃዎችን ለመለዋወጥ የሚያስችላቸውን አህጉራዊ ወታደራዊ ትብብሮች በጋራ ሲሰሩ ቆይተዋል።

ከጸጥታው ዘርፍ ባሻገር፣ በኢኮኖሚ ትስስር ረገድ ኢትዮጵያ ለኬንያ የምታቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የሳፋሪኮም በኢትዮጵያ እያደረገ ያለው ሰፊ የዲጂታልና የፋይናንስ ኢንቨስትመንት እንዲሁም የቀልጣፋ የድንበር ንግድ ሥርዓት (Simplified Border Trade Regime) ትግበራ የሁለቱን አገራት ሕዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት በተግባር ያረጋገጡ ዋነኛ የትብብር መስኮች ናቸው።

የሀገራቱ መሪዎች የሚያደርጓቸው ተከታታይ የጉብኝት ልውውጦች ለዚህ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጨማሪ ጥንካሬን ፈጥረዋል።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እ.ኤ.አ በ2022 በአዲስ አበባ ያደረጉት ጉብኝት እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእ.አ.አ የካቲት 2024 የኬንያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በቱሪዝም፣ በኢነርጂና በባህል ዘርፎች በርካታ የመግባቢያ ስምምነቶች እንዲፈረሙ በር ከፍተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የሁለቱ አገራት ከፍተኛ የጦር አዛዦች (ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ጄኔራል ቻርለስ ካሃሪሪ) ሽብርተኝነትን ለመከላከልና ለድንበርና ለአካባቢው ደህንነት መጠበቅ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ባለፈው ዓመት መስከረም ወር ላይ መፈራረማቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ የመሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓትን ለመካፈል ዛሬ ጠዋት ኬንያ መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ይህ ሁለቱ ሀገራት ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጎልበት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በላሙ ወደብ መነሻነት የሚገነባውን ባለ 16 ቢሊዮን ዶላር የዳንጎቴ ግሩፕ የነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመታደም ኬንያ መገኘታቸው፣ ሁለቱ አገራት ለላፕሴት (LAPSSET) ኮሪደር ፕሮጀክት ያላቸውን የማይናወጥ አቋም ያሳያል።

የኢትዮጵያና የኬንያ ቀጣይ ትብብር የምሥራቅ አፍሪካን አጠቃላይ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ምህዳር የመቀየር አቅም አለው።

የላፕሴት የኮሪደር የባቡር፣ የሀይዌይና የነዳጅ ቧንቧ መስመሮች ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ የሀገራቱን የንግድና የኢንቨስትመንት ልውውጥ የበለጠ የሚያሳድግ ሲሆን ይህም ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብር ተምሳሌት የሚሆን ነው።

ይህ በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስና በጋራ ብልጽግና መርህ ላይ የተመሰረተው አጋርነት፣ የአፍሪካውያን መፍትሔ ለአፍሪካ ችግሮች የሚለውን መርህ በተግባር በመተርጎም፣ የቀጣናውን ዘላቂ ሰላም፣ ደህንነትና ልማት በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

Tags: EthiopiaKenyaPan-Africanism
ShareTweetShare
Previous Post

የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ ቀጣናዊ ፋይዳው የጎላ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Next Post

በአዲስ አበባ እና አከባቢው ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውንም ድሮን ለማብረር ፍቃድ እንደማይሰጥ ተገለፀ

Related Posts

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ
#ethiopia

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
11
የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር
Analysis

የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር

November 16, 2026
10
“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ
Analysis

“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ

November 16, 2026
20
ምርኮኞቹ ጀነራሎች ያጋለጡት የህወሓት ሴራ
Analysis

ምርኮኞቹ ጀነራሎች ያጋለጡት የህወሓት ሴራ

November 14, 2026
57
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ብሔራዊ ጥቅም ማለት መንግስትን መደገፍ አይደለም!
Analysis

ሚዲያዎችና ብሄራዊ ጥቅም

November 11, 2026
22
Next Post
በአዲስ አበባ እና አከባቢው ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውንም ድሮን ለማብረር ፍቃድ እንደማይሰጥ ተገለፀ

በአዲስ አበባ እና አከባቢው ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውንም ድሮን ለማብረር ፍቃድ እንደማይሰጥ ተገለፀ

ሁቲን ማስቆም ያልቻለችው ግብፅ! _ NBC አለም-አቀፍ

ሁቲን ማስቆም ያልቻለችው ግብፅ! _ NBC አለም-አቀፍ

የአማራ፣ የሶማሌ እና የሲዳማ ክልል ምክር ቤቶች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

የአማራ፣ የሶማሌ እና የሲዳማ ክልል ምክር ቤቶች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?