
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሳ በአራዳ ክፍለ ከተማ በምርጫ ክልል 2/14 ወረዳ 8 ሸማቾች ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እየተካሄደ ሲሆን ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሳ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሸማቾች ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
ለጋዜጠኞች ማብራሪያ የሰጡት ፕሬዝዳንቱ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት የተመዘገቡበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከቀደሙት ምርጫዎች የተለየ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።
ከፍተኛ የህዝብ ቁጥርም በስፍራው በመገኘት ድምጽ እየሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል።
እንደማንኛውም ዜጋ ድምጽ መስጠታቸው የጠቆሙት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ድምጽ መስጠት ዋጋ እንዳለው ተናግረዋል።
በ-ሰላም ይልማ












