Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Entertainment

ያለ አስተማማኝ አህጉራዊና ቀጣናዊ ሰላም ልማትና ዕድገትን ማረጋገጥ አይቻልም – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

ያለ አስተማማኝ አህጉራዊና ቀጣናዊ ሰላም ልማትና ዕድገትን ማረጋገጥ አይቻልም - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

May 30, 2026
in Entertainment
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

May 30, 2026

ያለ አስተማማኝ አህጉራዊና ቀጣናዊ ሰላም ልማትና ዕድገትን ማረጋገጥ እንደማይቻል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለፁ። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በሞዛምቢክ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም በጄኔራል ጁሊዮ ዶ ስሳንቶስ ጃኔ ከተመራ ልዑክ ጋር ኢትዮጵያና ሞዛምቢክ ካሁን ቀደም የተፈራረሙትን የሁለትዮሽ ወታደራዊ ትብብር ስምምነት ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማድረስ ያለመ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ባደረጉት ውይይት ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንደገለጹት ኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው ታሪካዊ ግንኙነትም በ”ፓን-አፍሪካኒዝም” መርሆዎች፣ አንድነት እና ጽናት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ተናግረዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ምዕራፍ መሸጋገሩን የገለጹት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው በወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት መጠናከር የቀጣናውን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ያለ ሠላምና ፀጥታ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትና ብልፅግናን ማሳካት እንደማይቻል ገልጸው ሽብርተኝነትን በጋራ በመዋጋት፣ በሳይበር ደኅንነትና መሠል የትብብር መስኮች ዙሪያ በቅንጅት በመስራት አህጉራዊና ቀጣናዊ ሠላምን ለማረጋገጥ በጋራ መቆም እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

የሞዛምቢክ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ጁሊዮ ዶ ስሳንቶስ ጃኔ በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራት በልዩ ልዩ የወታደራዊ ትብብር መስኮች ዙርያ በጋራ መስራታቸው ለአህጉራዊና ቀጣናዊ ሰላም መረጋገጥ የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጄኔራል ጁሊዮ ዶ ሳንቶስ ጃኔ አክለውም ከአትዮጵያ ጋር በዘርፈ ብዙ ወታራዊ የትብብር መስኮች ዙሪያ በቅንጅት መስራታችን በትምህርት እና ስልጠና ሰፊ ልምድ እና ተሞክሮ ለማግኘት ያስችልናል ብለዋል፡፡

የመከላከያ ውጪ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ የተካሄደው የሁለትዮሽ መድረክ ሀገራቱ ከአሁን ቀደም የተፈራረሙትን ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ወደ ተግባር የቀየረና ቀጣይ በሚሰሩ የትብብር ማዕቀፎች ዙሪያ አቅጣጫ ያስቀመጠ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና ልማት መረጋገጥ ካላት ቁርጠኝነት የተነሳ ሞዛንቢክን ጨምሮ በርካታ ሀገራት በተለያዩ ወታደራዊ ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እያሳዩ እንደሚገኙም መግለጻቸውን ኢዜአ ከመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

Source: @NBCEthiopia
Via: NBC Ethiopia
Tags: #addisababaEthiopiaEthiopianElection2018FacebookMetaምርጫ2018
ShareTweetShare
Previous Post

7ተኛው የኢትዮጵያ ምርጫ ለመላው አፍሪካ ትልቅ ትርጉም አለው – ኡሁሩ ኬንያታ

Next Post

7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ 2018 | የቀጥታ ስርጭት | Live | Ethiopia

Related Posts

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ
#ethiopia

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
8
ኢትዮጵያ እና የወፍ ሀብቷ
Bussines

ኢትዮጵያ እና የወፍ ሀብቷ

November 11, 2026
25
ከአንድ ደቂቃ በላይ በጣቶቹ በመቆም ሪከርድ የሰበረው አሜሪካዊ
Entertainment

ከአንድ ደቂቃ በላይ በጣቶቹ በመቆም ሪከርድ የሰበረው አሜሪካዊ

November 1, 2026
23
COP 32 ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ዕድገት
Entertainment

COP 32 ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ዕድገት

October 27, 2026
21
አዲሲቷ አዲስ አበባ ላይ ያተኮረ የፎቶና የቪዲዮ ውድድር የመጨረሻ ዙር!
Entertainment

አዲሲቷ አዲስ አበባ ላይ ያተኮረ የፎቶና የቪዲዮ ውድድር የመጨረሻ ዙር!

October 5, 2026
13
🔴የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ከመስቀል አደባባይ የቀጥታ ሥርጭት @NBCETHIOPIA ​
Entertainment

🔴የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ከመስቀል አደባባይ የቀጥታ ሥርጭት @NBCETHIOPIA ​

September 26, 2026
16
Next Post
7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ 2018 | የቀጥታ ስርጭት | Live | Ethiopia

7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ 2018 | የቀጥታ ስርጭት | Live | Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ድምጻቸውን ሰጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ድምጻቸውን ሰጡ።

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ድምጽ ሰጥተዋል ።

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ድምጽ ሰጥተዋል ።

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?