
በአዳማ ከተማ በ43 ቢሊዮን ብር የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።
ፕሮጀክቶቹ የምግብ ሉዓላዊነትንና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ፣ የቤተሰብ ኑሮን ለማሻሻል፣ የስራ ባህልን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው መሆኑ ተገልጿል።
ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል ዳታ ሴንተር፣ የከብት ማደለቢያ፣ የዶሮ ማርቢያ ሼዶች እና የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች ይገኙበታል።
ፕሮጀክቶቹ በህዝብ እና በመንግስት ተሳትፎ የተገነቡ መሆናቸውን የአዳማ ከተማ ከንቲባ ሀይሉ ጄልዴ ገልጸዋል።
ፕሮጀክቶቹ ለበርካታ ነዋሪዎች የስራ እድልን የፈጠሩ እና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የሚረዱ ናቸውም ተብሏል።
በ-የአብስራ ብርሃኑ












