Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን አደረሳችሁ ሙሉ መልዕክት! ​

ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን አደረሳችሁ ሙሉ መልዕክት! ​

March 19, 2026
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ዒድ አል ፈጥር የበረከት በዓል ተደርጎ ይታመናል። ሮመዳንም የአላህ (ሱወ) ደግነት የሚገለጥበት፣ ውድ ስጦታዎችን ለሰው ልጆች የሰጠበት ወር ነው። ቁርአን ወደ ምድር የወረደበት፣ ጀሃነም ተዘግቶ የጀነት በሮች የሚከፈቱበት፣ ሁሉም እንደ እምነቱ ጽናትና እንደ አላህ (ሱወ) እዝነት ምናዳዎችን የሚያገኝበት ወቅት በመሆኑ ሕዝበ ሙስሊሙ ዘወትር የሮመዳንና ዒድ አል ፈጥርን መምጣትን በጉጉት ይጠብቃል።

በዒድ አል ፈጥር ከፈጣሪ በረከት የሚቸራቸው የሮመዳንን ወር በፆምና በዱዓ ያሳለፉት ናቸው፤ በበዓሉ መምጣት የሚያደሰቱትም ሮመዳንን በመልካም ተግባር ለማሳለፍ የበረቱ ናቸው። በተቀደሰው ወር ከክፋት የተቆጠቡ፤ ለድኾችና አቅመ-ደካሞች ዘካት የሰጡ፤ የበደሏቸውን ይቅር ለማለት የደፈሩ በሐሴትና በመንሳዊ ኃይል ተሞልተው ለዒዱ ይደርሳሉ። በተቃራኒው ለዱዓ የሰነፉና ለመስጠት የሰሰቱ ከፈጣሪ በረከት አያገኙም።

ከፊታችን ግንቦት ላይ የሚካሄደው ምርጫ ሀገራችንን የዴሞክራሲን ድል የምትቀዳጅበት፣ ወደ ቀጣይ ብሩህ ዘመንዋ የምትሸጋገርበት በር ነው። እንደ ሀገር ለዓመታት ዴሞክራሲን ስንናፍቅ ኖረናል። ጉዞአችን አልጋ በአልጋ አልነበረም። ነገር ግን ከፈተና በሁዋላ በረከት፣ ከብርታት በኋላ ሐሴት እንዳለ ከሮመዳን ጾምና ከዒድ አል ፈጥር በዓል እንማራለን።

መልካም የዘራ ሰው መልካም ምርት እንደሚያጭድ ሁሉ፤ እሾክ የዘራውም አሜኬላ ያጭዳል። ስለተመኘን ብቻ አሜኬላው በመልካም ሰብል አይለወጥም። በመንፈሳዊውም ሆነ በዓለማዊ ጉዳዮች ውስጥ ዘርና ምርት የተቆራኙ ናቸው። ስለዴሞክራሲም ስናስብ ይሄንን ሐቅ መዘንጋት የለብንም። የምንገነባው ሕጋዊና ሕዝባዊ መንግሥት የሚወሰነው በቅድመ ምርጫ ተሳትፎአችን ልክ ነው። ተሳትፎአችን ከጠየመ ዴሞክራሲያችንም ይጠይማል። ደካማ ተሳትፎ አድርገን ጠንካራ ዴሞክራሲ ለማዋለድ መመኘትም ሞኝነት ነው። ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በባዶ መሬት አይበቅልም፤ በግጭትና ሥርዓት አልበኝነትም አይገነባም። ይልቁንም ስክነትን፣ ለትብብርና ቅንጅት ልብን ክፍት ማድረግን፣ በጨዋታው ሕግ መመራትን ይጠይቃል።

ሮመዳን ቤተሰብ የሚገናኝበት፣ ኅሊና የሚሰበሰብበት፣ ሰውነት የሚገራበት እና መንፈስ የሚቀናበት ወር ነው። ዒድ አል ፈጥር ደግሞ የሰውን ልጅ ጤናማ ግንኙነቶች የሚያመለክት በዓል ነው። የሰው ልጅ ከፈጣሪው ጋር፣ ከራሱ ጋር እና ከወገኑ ጋር የሚኖረው ግንኙነት ጤናማ ካልሆነ ጠቅላላ ሕይወቱ ጤናማ አይሆንም። በሮመዳን ወቅት ጾሙ ሰዎችን ከራሳቸው ጋር ያገናኛቸዋል፤ ሰላትና ዱአ ከፈጣሪያቸው ጋር ያገናኛቸዋል፤ አፍጣርና ዘካት ደግሞ ከማኅበረሰቡ ጋር ያገናኛቸዋል። ኢትዮጵያውያን ጤናማ ሕይወትን መምራት እንድንችል እነዚህን ሦስቱን ጤናማ ማድረግ አለብን።

ሰው ከፈጣሪው እና ከራሱ ጋር ያለው ግንኙነት ጤናማ ካልሆነ ለማኅበረሰብም ለሀገርም ጠንቅ ነው። ሰው ከራሱ ጋር እየተጋጨ ከኖረ ከሁሉም ጋር ይጋጫል። ዛሬ ጦርነትን ባህል፣ ዝርፊያን ልማድ፣ ጥፋትን ዕሴት፣ ውድመትን ክብር አድርገው የሚኖሩት ሰዎች የመጀመሪያው ችግራቸው ከፈጣሪያቸውና ከራሳቸው ጋር አለመስማማት ነው። ውስጣዊ ባሕርያቱ ያልተስማሙለት ሰው ከማንም ጋር አይስማማም። ዕርቅ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ መግባባት እና መስማማት የሚባሉት ነገሮች አይገቡትም።

ሰው ከፈጣሪውና ከራሱ ጋር ከተስማማ፣ ከማንም ጋር መስማማት ይችላል። ከእንስሳትም ጋር ሳይቀር። “ለድንቢጥ እንኳን ቢሆን የራራ ሰው፤ በፍርድ ቀን (ቂያማህ) አላህ ይራራለታል” ሲሉ ነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያስተማሩት ለዚህ ነው። የእስልምና ዋናው መሠረቱ ሰላም የሆነው ለዚህ ነው። ሰላም ማለት ከራስና ከአካባቢ ጋር በጤናማ ግንኙነት ለመኖር መቻል ነውና።

የዘንድሮውን የዒድ በዓል ስናከብር በዓለማችን ስለ ሰላም የሚነገረውን ያህል የዓለም ሕዝቦች በሰላም መኖር ለምን አልቻሉም ብለን እንጠይቅ? የግጭትና የጦርነት ድንጋይ እየደጋገመ ለምን ይመታናል? ከአዛኝ ይልቅ ገዳይን እንደ ጀግና የሚያየው ልምምዳችን ለምን ገናና ሆነ? የሰው ልጅ ከግጭትና ከጦርነት ያተረፈው ድህነትና ኋላ ቀርነት መሆኑን እያየን ለምን አልተማረንም? ሠልጥኗል በምንለው ዓለም የሚኖሩ ወገኖቻችን እንዴት ግጭትንና ጦርነትን የሚያበረታቱ ሆኑ? ይህ ትውልድ እነዚህን ጥያቄዎች በሚገባ አጢኖ ምላሽ ሊያገኝላቸው ይገባል።

ከራሳቸው ጋር ሰላም ያጡ አካላት የማኅበረሰቡን ሰላም እንዲረብሹ ልንፈቅድላቸው አይገባም። ከሮመዳን ዕሴቶች ጋር የተጣሉ ሰዎች ዘመኖቻችንን እንዲረብሹ ልንፈቅድላቸው አይገባም። በዐሥራ ሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደ ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን መኖር ቀድሞ መገኘት ነው። በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን እንደ ዐሥራ ሁለተኛው ክፍለ ዘመን መኖር ግን መረገም ነው። መግደል፣ ማገት፣ የገበሬውን እርሻ ማቃጠል፣ ሴቶችን መድፈር፣ ማኅበራዊ ተቋማትን መመዝበር፣ ቅርስና ታሪክን ማበላሸት፣ ጠመንጃን የሁሉም ነገር መድኃኒት አድርጎ መውሰድ፣ እነዚህ ሁሉ ከ800 ዓመታት በፊት ያለፉ የሰው ልጅ ጠባያት ናቸው።

ከሦስት አካላት ጋር የታረቁ ሰዎች ብርቱዎች ናቸው ይባላል፤ ከራሳቸው፣ ከማህበረሰባቸው እና ከፈጣሪያቸው ጋር። እንደ ኢትዮጵያዊ እኛም ራሳችንን የገዛን፣ ፈጣሪን የምንፈራ እና ለማህበረሰብ ሰላምና እድገት የምንጨነቅ መሆን አለብን። ኢትዮጵያ የምታድግና የምትበለጽገው በዜጎችዋ እንጂ በሌላ አይደለም። ዜጎችዋ ሲገነቡ ትገነባለች፤ ዜጎችዋ ሰላም ሲሆኑ ሰላም ትሆናለች፤ ዜጎችዋ ሲስማሙ የብልጽግና ጉዞዋ ይሰምራል። የኢትዮጵያም መበልጸግ የሌላ ሳይሆን የእኛ መበልጸግ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያ እንድትበለጽግ የሚፈለግብንን መሥዋዕትነት ሁሉ የመክፈል ኃላፊነት የእኛ ነው። የእኛ ልፋት ከዛሬ አልፎ ለትውልድ ይተርፋል። ሀገር መውደዳችን የሚታወቀው እና መልካም ዜግነታችን የሚገለጠው በሥራችን ነው። ነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) “ምርጥ ሰዎች ማለት ሌሎችን ለመጥቀም የበረቱ ሰዎች ናቸው” ብለው ያስተማሩትም ለዚህ ነው። ይሄን የዒድ አል ፈጥር በዓል እነዚህን መልካም ዕሴቶች እያሰብን፣ ሦስቱን ጤናማ መሥመሮችንም እያጸናን እንድናከብረው አደራ እላለሁ።

በድጋሚ መልካም የዒድ አል ፈጥር በዓል ይሁን!

ዒድ ሙባረክ!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!

መጋቢት ፣ 2018 ዓ.ም

Source: @NBCETHIOPIA
Via: NBC ETHIOPIA
Tags: Eid al_FitrEthiopiaPM Abiy Ahmed
ShareTweetShare
Previous Post

የመጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም የኤንቢሲ ኢትዮጵያ የምሽት ዜናዎች

Next Post

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

የ1447ኛው የኢድ ሰላት ከአዲስ አበባ ስታዲየም የቀጥታ ስርጭት | Live | Ethiopia ‪

የ1447ኛው የኢድ ሰላት ከአዲስ አበባ ስታዲየም የቀጥታ ስርጭት | Live | Ethiopia ‪

በዩኔስኮ የተመዘገበው ሹዋሊድ በዓል የዘንድሮን አከባበር አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

በዩኔስኮ የተመዘገበው ሹዋሊድ በዓል የዘንድሮን አከባበር አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?