
በጀርመን የኤሌክትሪክ ኃይል እሚያመነጩ አዳዲስ ሶላር አጥሮች (Solar Fences) ተመራጭ እየሆኑ መጥተዋል።
እነዚህ አጥሮች እንደ መደበኛ አጥር ግቢን ከመከለላቸውም በላይ፣ በሁለቱም በኩል የፀሐይ ብርሃን መቀበል የሚችሉ (Bifacial) ዘመናዊ ፓነሎች ናቸው።
ፓነሎቹ ቀጥ ብለው (Vertical) የሚተከሉ በመሆናቸው፣ በተለይም የፀሐይ ብርሃን ዝቅ ባለበት የጧትና የከሰዓት ሰዓታት ላይ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫሉ።
እንደ ጣሪያ ላይ ፓነሎች በበረዶ የመሸፈን ዕድላቸው አነስተኛ በመሆኑ፣ በብርድና በክረምት ወቅት ያለማቋረጥ ኃይል መስጠት ይችላሉ።
ምንም እንኳን የመጀመሪያ መትከያ ዋጋቸው ከፍ ቢልም፣ በረጅም ጊዜ ግን የሚያመነጩት ኃይል የኤሌክትሪክ ወጪን ስለሚቀንስ ከእንጨት አጥር የበለጠ ርካሽ ያደርጋቸዋል።
ይህ ቴክኖሎጂ ማንኛውንም ክፍት ቦታ ወደ ኃይል ምንጭነት መለወጥ እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ነው ተብሎለታል።
በ – ዳንኤል መኮንን
Source:
@NBCETHIOPIA
Via:
NBC ETHIOPIA












