
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው ፦
“በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ትብብር በ”Timbuktoo Initiative” አማካይነት የተገነባውን AI UniPodን ዛሬ ይፋ አድርገናል።
ይህ የፈጠራ ማዕከል እውን መሆኑ ኢትዮጵያን ከቴክኖሎጂ ጥገኝነት ወደ ቴክኖሎጂ ፈጣሪነት በማሸጋገር ረገድ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ታላቅ እርምጃ ነው።
በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሉዓላዊነት ማለት የራስን ዳታ መቆጣጠር፣ የራስን የዲጂታል ቀመር መቅረጽ እና የራስን ችግር በራስ መፍትሄ መፍታት ማለት ነው። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ የመጪ ዘመን መዳረሻዋን በራሷ እየሠራች ነው።
እኛ የወደፊቱን እጣ ፈንታችንንና መዳረሻችንን ሌሎች እንዲወስኑ አንጠምብቅም፤ ይልቅስ እዚሁ በሀገራችን ጥበብ፣ በራሳችን እውቀት እንቀርጸዋለን።
ይህ ተነሳሽነት ከዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እና ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳችን ጋር የተጣጣመ ሲሆን፣ ለወጣቶቻችን የፈጠራ ላቦራቶሪ፣ ለቴክኖሎጂ ፈጣሪዎቻችን የመጎልበቻ ማዕከል፣ ለአጋሮቻችን ደግሞ በጋራ የመሥራት ውጤት ትልቅ ማረጋገጫ ነው።
አፍሪካ መፃኢ ብሩህ ተስፋዋን በራሷ ትገነባለች፤ ኢትዮጵያም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መሪ ትሆናለች!” ሲሉ በማህበራዊ የትትስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡











