Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

“ዘላቂ ሰላምን እና ልማትን ለማረጋገጥ ሕዝቡ ፅንፈኞችንና ተላላኪወችን የሚሸከምበት ትክሻ እንደሌለው በሕዝባዊ የውይይት መድረኮች አረጋግጧል” የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

"ዘላቂ ሰላምን እና ልማትን ለማረጋገጥ ሕዝቡ ፅንፈኞችንና ተላላኪወችን የሚሸከምበት ትክሻ እንደሌለው በሕዝባዊ የውይይት መድረኮች አረጋግጧል" የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

January 2, 2026
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

January 2, 2026

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የክልሉ ሕዝብ ያገኘዉን ሰላም በማፅናት አይቀሬውን የሀገሪቱን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን እየሠራ መሆኑን አስታውቋል። የክልሉ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ የሰጠው ሙሉ መግለጫ ቀጥሎ ቀርቧል።

የአማራ ሕዝብ በሥርዓተ መንግሥት ምስረታና በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን እህት ወንድም ሕዝቦች ጋር በመሆን ለኢትዮጵያ አንድነት አወንታዊ ድርሻዉን የተወጣ ሕዝብ ነው።

ሕዝባችን በርካታ አኩሪ ታሪኮች ያሉት፤ ከክልሉ ባለፈ የሀገራችን ሕዝቦች ቋንቋቸው፣ ሃይማኖታቸው እና ማንነታቸው ተከብሮ፤ በመቻቻልና በአብሮነት እንዲኖሩ የሠራ ታላቅ ሕዝብ ነው፡፡

ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታትም ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ሰባዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቹ ተከብረውለት በነፃነት እንዲኖር በተካሄደው የለውጥ ጉዞ የክልሉ መንግሥት እና ሕዝብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳደረጉ የሚታወቅ ሃቅ ነው፡፡ በተለይም በተሳሳተ ትርክት ሕዝባችንን ዋጋ ሲያስከፍሉ የቆዩ ግፈኞችን ከሌሎች የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ጋር በጋራ ታግሎ በሀገራችን ታሪካዊ ለውጥ እንዲመጣ የታገለ ሕዝብ ነዉ፡፡ በሂደቱም ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ፖለቲከኞች እንዲሁም ሌሎች የለውጡ መሪ የነበሩ ኃይሎች ድርሻቸዉ በታሪክ የሚቀመጥ ነው። በሀገራችን የተገኘዉን ለውጥም በለውጥ ፈላጊ ኃይሎች የተባበረ ክንድና በሕዝብ ከፍተኛ ድጋፍ ማስቀጠል ተችሏል፡፡

ይሁን እንጂ ለውጡን ለማፅናት እና ለማስቀጠል መንገዶቹ ሁሉ አልጋ በአልጋ አልነበሩም። ከለውጡ ጅማሮ አንስቶ የመንግሥትን ሆደ ሰፊነት እንደ ፍርሃት በመቁጠር ሕዝባችን ያገኘዉን ሁለንተናዊ ድል ለመቀልበስ መልከ ብዙ ፈተናዎችና ጠመዝማዛ መንገዶች ታልፈዋል፡፡ በሴራ ፖለቲካ ተወልደው ያደጉ የውስጥ ባንዳዎችና የውጭ ባዕዳን በመቀናጀት ሀገራችንንና ክልላችንን በጦርነት ለማመስ ያልፈነቀሉት ድንጋይ፣ ያልቆፈሩት ጉድጓድ የለም ብሎ በድፍረት መግለጽ ይቻላል፡፡ በተለይ ደግሞ ባለፉት ሁለት ዓመታት በክልላችን ፅንፈኛ ቡድኖች የአማራን ሕዝብ ትክክለኛ ጥያቄዎች እንደሽፋን በመጠቀም ወደ ግጭት በመግባት በሕዝብ ላይ ከባድና አሳፋሪ ሰባዊና ቁሳዊ ጉዳት አድርሰዋል፡፡

ይህ ቡድን የሕዝብ መጠቀሚያ መሰረተ ልማቶችን አውድሟል፤ የነገ ሀገር ተረካቢ ትዉልድ እንዳይኖር የትምህርት ሥርዓቱን አስተጓጉሏል፤ መምህራንን ገድሏል፤ የሚማሩ ህጻናት ላይ ቦምብ በመጣል ጉዳት አድርሷል፤ ከራሱ ሃሳብ ጋር አልሄዱም ያላቸውን ሁሉ በሃሳብ ልዩነት ብቻ ረሽኗል፤ የሀገር ሽማግሌዎችንና የሃይማኖት አባቶችን ገድሏል፤ ሰው የሆነ ፍጡር ያደርገዋል ተብሎ የማይታሰብ ድርጊት በጭካኔ እጅ እና ጆሮ በመቁረጥ የአረመኔነቱን ጥግ በአደባባይ አሳይቷል፣ ትርፍ አምራቹ አርሶ አደር ያመረተዉን ለገበያ እንዳይሸጥ እና ግብአት እንዳይቀርብለት ከልክሏል፤ የምርትና አገልግሎቶችን እንቅስቃሴ ገድቧል፣ እገታ እና መሰል የሽብር ተግባራትንም በስፋት ፈፅሟል።

ይህ የሽብር ተግባር የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን በተቀናጀ መልኩ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ክልሉን በልዩ ልዩ የሴራ መንገዶች ማዳከም በሚል የሚከተለው እቅድ መሆኑ በግልፅ ሁሉም ሊገነዘበውና ሊታገለው ይገባል፡፡ ይህንን አፍራሽ እቅዱን ለማሳካት ጦር መሣሪያ በማስታጠቅ፣ ወታደራዊ ድጋፍ በመስጠት፣ በፕሮፖጋንዳ በማገዝ፣ በፋይናንስና በሚዲያ በመደገፍ በተቀናጀ መልኩ ታስቦበት የተሠራና የአማራን ሕዝብ መሪ አልባ እንዲሆንና አንድነት እንዳይኖረው በማድረግ እርስ በርሱ እንዲባላ የተሸረበ እኩይ ሴራ ነው፡፡

ይሄን እኩይ የፅንፈኞች ድርጊትና ተግባር ለመቀልበስም መንግሥት ከታታሪው፣ ከአርቆ አሳቢውና ከሰላም ወዳዱ የክልላችን ሕዝብ ጋር በመሆን በወሰደዉ ሕግ የማስከበር እርምጃ የፅንፈኞችና የላኪዎቻቸውን ህልም በማክሸፍ ሕዝባችን የሰላም አየር መተንፈስ ጀምሯል።

ክልሉን በሁሉንተናዊ መልኩ የማዳከም ፕሮጀክት ያላቸው ባንዳዎችንና ባዕዳንን የፌደራልና የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት አስፈላጊውን ዋጋ ሁሉ በመክፈል ውድ የሆነውን ሰላም በማረጋገጥ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ አንፃራዊ ሰላም እንዲመጣም የጥምር ፀጥታ ኃይላችን አኩሪ ገድል በታሪክ ሲዘከር የሚኖር ነው፡፡

ስለሆነም ከምንም በላይ የተጀመረውን የልማትና የብልፅግና ጉዞ ለማስቀጠልና የአማራን ሕዝብ ሁለተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የክልሉ መንግሥት ከምንጊዜውም በላይ ርብርብ እንደሚያደረግ፤ አክራሪነትና ፅንፈኝነት ለራሱ ለፅንፈኛውም የማይበጅና የተሸናፊዎች መንገድ በመሆኑ ችግሮችንም በውይይትና በሰላም ለመፍታት የክልሉ መንግሥት ምንጊዜም ለሰላም የዘረጋዉ እጁ የማይታጠፍ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ታጥቀው ጫካ ሲንንቀሳቀሱ የነበሩ በሺህ የሚቆጠሩ ሃይሎችም የክልሉን መንግሥት የሰላም ጥሪ ተቀብለው በመግባት እና ወደ ኅብረተሰቡ በመቀላቀል መደበኛ ሕይወታቸዉን እንዲመሩ ማድረግ ተችሏል። ይሄ የሰላም ጥሪ አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑንም ለማሳወቅ እንወዳለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ተጠናክሮ የቀጠለው የፅንፈኞች ተግባር ለአማራ ሕዝብ ከፍተኛ በደል እያስከተለ መሆኑንና ታጣቂው ከአማራ ሕዝብና ከኢትጵያ ጠላቶች ጋር በመቀናጀት ሀገር ለማፍረስ በተላላኪነት እያገለገለ መሆኑን የተረዱ ወጣቶችና ቡድኖች መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ እየተቀበሉ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት መንግሥት ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ዝግጁነት ውጤት ነው፡፡

መንግሥታችን የገጠሙትን ፈተናዎች ሁሉ ተጋፍጦና ተቋቁሞ እንደ ክልል በልማት፣ በሰላምና በልዩ ልዩ ተግባራት በተለየ እምርታዊ ጉዞ ውስጥ ለመግባት ጥረትም አድርጓል፡፡ ተጨባጭ ለውጥም ማስመዝገብ ችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅትም የክልሉ መንግሥት የአጭርና የረዥም ጊዜ ስትራቴጅክ ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደሥራ በመግባት፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በሳይንስና ቴክኖሎጅ ዘርፎች ዕምርታዊና ተመጋጋቢ ዕድገት በገጠርና በከተማ ለማስመዝገብ ዓልሞ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ በትምህርትና በጤናው ዘርፍም የላቀ ለውጥ ለማምጣት ክፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በግጭት ምክንያት ተስተጓጉለው የነበሩ ትምህርት ቤቶችም ተከፍተው ተማሪዎቻቸውን በማስተማር ላይ ይገኛሉ፡፡

እየተመዘገቡ ያሉ ተስፋ ሰጭ የልማት ውጤቶችም አሉ፡፡ የከተሞች የኮሪደር ልማት፣ የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በበጋ ስንዴ ልማት፣ የስሚንቶ ፋብሪካዎች— ወ.ዘተ. በቂ ማሳያዎች ናቸው፡፡

ከሥራ አጥነት እና ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዘው ከሕዝባችን የሚነሱ ችግሮችንም ለመፍታት ከመቼውም ጊዜ በላይ በአገልጋይነት መንፈስ ጠንክረን እየሠራን እንገኛለን።

በአጠቃላይ መንግሥት የሕግ ማስከበሩን ተግባር አጠናክሮ ከማስቀጠል ጎን ለጎን የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም ይበልጥ ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ በሰላማዊ ውይይቶች ችግሮችን የመፍታት አማራጭን በመከተል ልማትንና ጥራት ያለው የሕዝብ አገልግሎት አሠጣጥ ሥራዎችን ለማስቀጠል በከፍተኛ ትኩረት የሚሠራበት ጉዳይ ይሆናል፡፡

በመሆኑም ዘላቂ ሰላምን እና ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ሕዝቡ ፅንፈኞችንና ተላላኪወችን የሚሸከምበት ትክሻ እንደሌለው በተደረጉት ትልልቅ ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች ያሳየበትን አቋሙንና የጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እናቀርባለን፡፡

አሁንም ድረስ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ወደጎን በመተዉ የክልላችንን ሰላም ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ሃይሎችን የማንታገስና የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር የሆነዉን ሕግ የማስከበር ተግባር አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑንም ለማሳወቅ እንወዳለን።

በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በሀሰተኛ መረጃዎች ሳይደናገሩ በሀገራችንና በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍንና የማይቀረውን የልማትና የብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ በምናደርገው ርብርብ የበኩላቸውን አወንታዊ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ

ታኅሣሥስ 2018 ዓ.ም

Source: @NBCEthiopia
Via: NBC Ethiopia
Tags: #addisababaAmhara regionEthiopiaFacebook
ShareTweetShare
Previous Post

የታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የኤንቢሲ ኢትዮጵያ የቀን ዜናዎች

Next Post

“አሜሪካ ተኩስ ከፈተችብኝ” ቬንዙዌላ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
“አሜሪካ ተኩስ ከፈተችብኝ” ቬንዙዌላ

"አሜሪካ ተኩስ ከፈተችብኝ" ቬንዙዌላ

NBC ቅዳሜ የመዝናኛ ፕሮግራማችንን በቀጥታ ቴሌግራም ቻናላችን ይከታተሉን

NBC ቅዳሜ የመዝናኛ ፕሮግራማችንን በቀጥታ ቴሌግራም ቻናላችን ይከታተሉን

ከ100ሺ በላይ ህጻናትን ተጠቃሚ እያደረገ ያለው ዋቢ የህጻናት መርጃ እና የትምህርት ማዕከል NBC ቅዳሜ  

ከ100ሺ በላይ ህጻናትን ተጠቃሚ እያደረገ ያለው ዋቢ የህጻናት መርጃ እና የትምህርት ማዕከል NBC ቅዳሜ  

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?