
የፕላስቲክ ከረጢቶችን(ፌስታሎችን)መጠቀም፣ ማምረትና ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት በወንጀል የሚያስጠይቀው አዋጅ ሊተገበር ነው።
አፈርን፣ ውሃ እና አየርን በመበከል በሰው ጤና ላይ ጉዳት የሚያደርስ አንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ለመከልከል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 ዓ.ም መፅደቁ አይዘነጋም።
አዋጁ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስርዓትን ለመዘርጋት እና የባለድርሻ አካላትን ሚና ለመለየት የሚያግዝም ነው ፡፡
በተመሳሳይ የአዋጁ መፅደቅ ተከትሎ በሐምሌ ወር በነጋሪት ጋዜጣ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮም ለአምራቾች፣ አስመጪዎች ፣ አከፋፋዮችና ተጠቃሚዎች የዝግጅትና የግንዛቤ የመፍጠሪያ ቀነ ገደብ ተቀምጧል።
ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ የፕላስቲክ ከረጢቶች ለቆሻሻ አያያዝ ስርዓት እንቅፋት እየፈጠሩ በመሆናቸው በባለፈው አመት መገባደጃ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዋጅ ክልከላ እንደተደረገባቸው በማስታወስ ለኤን ቢሲ ኢትዮጵያ ማብራሪያ የሰጡት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የከተማ ቆሻሻ እና አወጋገድ ክትትል ዴክስ ቡድን መሪ ዋሲሁን አለሙ ናቸው፡፡
አዋጁ በአጠቃላይ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀምን፣ማምረትን፣ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት፣መሸጥ፣ ማከፋፈል እና ማከማቸትን አዋጁ ሙሉ በሙሉ እንደሚከለክል ነው ብለዋል፡፡
በአዋጁ ክልከላ የተደረገባቸውን ምርቶች ማንኛውም ሰው ለመጠቀም መሞከርና መጠቀም ከ2ሺህ _5ሺህ ብር ቅጣት እንደሚዳረግ ገልጸዋል፡፡
አምራቾች፣ አስመጪዎች፣ አከፋፋዮች እና አከማቾች ደግሞ ከብር 50- 200 ሺህ ብር እና በአምስት አመት ጽኑ እስራት አዋጁ ደግጓል፡፡
ተኪ ምርት የማይገኝላቸው የአንድጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ የፕላስቲክ ከረጢቶች በልዩ ሁኔታ የሚፈቀድበት ስርዓትም በመመሪያ ተለይተው እንዲቀመጡ እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በባለስልጣኑ የከተማ ደረቅ ቆሻሻና አወጋገድ ክትትል ዴክስ መሪ ዋሲሁን አለሙ የአዋጁ ዋና አላማ ቆሻሻን ከምንጩ ለመቀነስ ነው ይላሉ።
ከመጪው የጥር 23/2018 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ሁሉም አካል ሊገነዘብ እንደሚገባው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስጠንቅቋል።
ክልከላ የተደረገባቸው የአንድጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ የፕላስቲክ ከረቲቶች ዝርዝር መመሪያዎች በባለስልጣኑ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል ። አያይዘውም ተኪ ምርት የማይገኝላቸው የፕላስቲክ ከረጢቶች በልዩ ሁኔታ የሚፈቀድበት ስርዓትም እንደሚኖር ፍንጭ ሰጥተዋል ።
በተለይም የአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ የፕላስቲክ ከረጢትቶችን የሚከለክለው አዋጅ ቁጥር 14/2017ን በተመለከተ ህብረተሰቡ እንዲገነዘበው ሲሉ አብራርተዋል።
ማህበረሰቡ እና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ይህንኑ ተገንዝበው አዋጁን ተግባራዊ በማድረግ ካለአስፈላጊ የገንዘብና እስር እንዳይዳረጉ ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።












